Lealem Tilahun/Hailenem Yemiyastateqegn/Eyewale Eyader

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሁሉን አድርገህልኛል የቀረብኝም የለም ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም (፪x)

አዝ እየዋለ እያደር ታምራትህ በዛ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ (፪x)

ምን እንልሃለን ማዳንህን እያየን ከምስጋና በላይ ምስጋናን እንሰዋለን ምን እንልሃለን ምሕረትህን እያየን ከክብርም በላይ ክብርን እንሰጣለን

የሰማይን ፀጋ የምድርን በረከት በሌላ እኮ አይደለም ባንተ ነው ያገኘሁት ጽድቅና ሰላምን የመንፈስን ደስታ አጎናጽፈኅኛል የሰራዊት ጌታ (፪x)

አዝ ሁሉን አድርገህልኛል የቀረብኝም የለም ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም

ምን ያጠያይቃል መልካምነትህ ለኔስ ጌታ ኢየሱስ በረከቴ ነህ መወደድ ስያንስህ ነው መች ይበዛብሃል እንኳን እኔነቴ ዘሬ ይገዛልሃል

እየዋለ እያደር ታምራትህ በዛ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ (፪x)

ምን እንልሃለን ማዳንህን እያየን ከምስጋና በላይ ምስጋናን እንሰዋለን ምን እንልሃለን ምሕረትህን እያየን ከክብርም በላይ ክብርን እንሰጣለን

መልካምን ማድረግ ማይታክትህ አቤት እግዚአብሔር ቸርነትህ አሃሃ ትላንት ያረከው ሳይበቃህ ዛሬም ደገምከኝ አብዝተህ (፪x)

በክብር ላይ ሌላ ክብር በክብር ላይ አሃ ቆርጫለሁ ለመጨመር ከዚያም በላይ አንደበቴን በምስጋና እየከፈትኩ ኦሆ ለድል ጌታ የድል ዜማን አመጣለሁ

ተራሮችንም ትክክል አደረክና እግዚአብሔር አሃ የነሃሱን ደጆች ሰባብረህ እኔን ለክብር አበቃህ (፪x)

በክብር ላይ ሌላ ክብር በክብር ላይ አሃ ቆርጫለሁ ለመጨመር ከዚያም በላይ አንደበቴን በምስጋና እየከፈትኩ ኦሆ ለድል ጌታ የድል ዜማን አመጣለሁ

አምላኬ መታመኛዬ ነው ጌታዬ ንጉሴ መደገፊያዬ ነው አምባዬ (፪x)