From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ:- ለእኔስ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም
ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው
በልቤ ፡ ከቶ ፡ አይበርድም (፪x)
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በልቤ ፡ የፈሰሰው
አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ መተኪያ ፡ የለው (፪x)
ብዙ ፡ ውሆች ፡ እንኩዋን ፡ ሊያጠፉት ፡ አልቻሉም
ግሩም ፡ ነው ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ አይነገርም
አዝ:- ለእኔስ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም
ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው
በልቤ ፡ ከቶ ፡ አይበርድም (፪x)
የብርሃን ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ መመኪያ
ፍቅርህ ፡ ሁሌ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ ከልቤ ፡ ማይጠፋ (፪x)
አንተን ፡ አንተን ፡ እንጂ ፡ ማንንም ፡ አልልም
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ እኔስ ፡ አልጠግብህም
አዝ:- ለእኔስ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም
ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው
በልቤ ፡ ከቶ ፡ አይበርድም (፪x)
የነፍሴ ፡ ጥጋብ ፡ የሕይወቴ ፡ አለኝታ
መጠጊያዬ ፡ ነህ ፡ ብሩኩ ፡ ጌታ (፪x)
ነፍሴን ፡ በምሕረትህ ፡ አድነሃልና
የመድህንቴ ፡ አምላክ ፡ ይድረስህ ፡ ምስጋና
አዝ:- ለእኔስ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም
ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው
በልቤ ፡ ከቶ ፡ አይበርድም (፬x)
|