ልቅረብህ (Leqrebeh) - ቅድስት ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቅድስት ፡ ካሳ
(Kidist Kassa)

Kidist Kassa 1.png


(1)

ተውድጃለሁ
(Tewedejalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2008)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:30
ጸሐፊ (Writer): ታምራት ክፍሌ
(Tamrat kifle
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቅድስት ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kidist Kassa)

አዝ፦ ልቅረብህ ፡ አብዝቼ ፡ ልወቅህ ፡ አብዝቼ
ልቅረብህ ፡ አብዝቼ ፡ ልወቅህ ፡ አብዝቼ
ያወኩ ፡ ለታ ፡ ወድሀለሁ ፡ ፈራሀለሁ ፡ እመስልኃለሁ
ያወኩ ፡ ለታ ፡ ወድሀለሁ ፡ ፈራሀለሁ ፡ እመስልኃለሁ

ዋላ ፡ ወደ ፡ ዉሃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ
ነፍሴን ፡ አንተን ፡ ተጠማች
አንተን ፡ ትናፍቅሐለች
አቅሜ ፡ ነህና ፡ ብርታቴ ፡ ነህና
ሁሌም ፡ ልቅረብህ ፡ ጌታ ፡ ፊትህ ፡ ልምጣና

አዝ፦ ልቅረብህ ፡ አብዝቼ ፡ ልወቅህ ፡ አብዝቼ
ልቅረብህ ፡ አብዝቼ ፡ ልወቅህ ፡ አብዝቼ
ያወኩ ፡ ለታ ፡ ወድሀለሁ ፡ ፈራሀለሁ ፡ እመስልኃለሁ
ያወኩ ፡ ለታ ፡ ወድሀለሁ ፡ ፈራሀለሁ ፡ እመስልኃለሁ

ካንተ ፡ ጋር ፡ የዋለ ፡ ክብርሕንም ፡ ያየ
መች ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ያሰኘዋል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይናፊቅኃል
ክብር ፡ አለዉ ፡ ፊትህ ፡ ግርማ ፡ ሞገስህ
ይፈሩኃል ፡ ያከብሩኃል ፡ አንተን ፡ ሚወዱ

አዝ፦ ልቅረብህ ፡ አብዝቼ ፡ ልወቅህ ፡ አብዝቼ
ልቅረብህ ፡ አብዝቼ ፡ ልወቅህ ፡ አብዝቼ
ያወኩ ፡ ለታ ፡ ወድሀለሁ ፡ ፈራሀለሁ ፡ እመስልኃለሁ
ያወኩ ፡ ለታ ፡ ወድሀለሁ ፡ ፈራሀለሁ ፡ እመስልኃለሁ

የእምነት ፡ አባቶቼ ፡ ለጽድቅ ፡ የጨከኑ
ላንተ ፡ ለመኖር ፡ ብቻ ፡ የወሰኑ
ወንጌሉን ፡ የእዉነት ፡ ያመኑ
ምድርን ፡ የናቁ ፡ ከኃጥያት ፡ የራቁ
ምሳሌ ፡ ሆነዉ ፡ አልፈዋል ፡ አንተን ፡ ያወቁ
ፊትህ ፡ ልምጣ ፡ ልፈልግህ ፡ ሰላሜ ፡ ያለዉ ፡ እግር ፡ ስር
ፊትህ ፡ ልምጣ ፡ ልፈልግህ ፡ ደስታዬ ፡ ያለዉ ፡ እግር ፡ ስር
ፊትህ ፡ ልምጣ ልፈልግህ ሰላሜ ያለዉ እግር ፡ ስር
ፊትህ ፡ ልምጣ ፡ ልፈልግህ ፡ ደስታዬ ፡ ያለዉ ፡ እግር ፡ ስር