ልጁ ፡ ነኝ (Leju Negn) - ቅድስት ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቅድስት ፡ ካሳ
(Kidist Kassa)

Kidist Kassa 1.png


(1)

ተውድጃለሁ
(Tewedejalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2008)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 3፡42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቅድስት ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kidist Kassa)

በኃጥያቴ ፡ በበደሌ ፡ ሙት ፡ የነበርኩ ፡ እኔ
አስቀድሞ ፡ ነበረብኝ ፡ ፍርድና ፡ ኩኔኔ
አሁን ፡ በመስቀሉ ፡ ስራ ፡ ዋጋ ፡ ተከፍሎልኝ
በክርስቶስ ፡ ተወደድኩኝ ፡ ልጁ ፡ ተደረኩኝ

አዝ፦ ልጁ ነኝ ፡ የሚወደኝ ፡ ሚረዳኝ ፡ ሚደግፈኝ
አልሄደም ፡ ካጠገቤ ፡ ፍቅር ፡ ነዉ ፡ ሁሌ ፡ ለእኔ

ለሰዉ ፡ ፍቅር ፡ ለመዋደድ ፡ ምክንያት ፡ ይፈልጋል
ዛሬ ፡ ወዶት ፡ ነገ ፡ ሲያድርጠላቱ ፡ ይሆናል
ማይለወጥ ፡ ማይቀየር ፡ ንፅህ ፡ ፍቅር ፡ ያለዉ
እዉነተኛ ፡ አባቴ ፡ ነዉ ፡ ፍቅር ፡ እየሱስ ፡ ነዉ

አዝ፦ ልጁ ነኝ ፡ የሚወደኝ ፡ ሚረዳኝ ፡ ሚደግፈኝ
አልሄደም ፡ ካጠገቤ ፡ ፍቅር ፡ ነዉ ፡ ሁሌ ፡ ለእኔ
ኦኦ…..ኦኦኦ…..ኦኦኦኦኦ……ልጁ
ነኝ…….ልጁ ነኝ……ልጁ ነኝ…….ልጁ ነኝ

አቅም ፡ ሳጣ ፡ ሲያዝል ፡ ልቤ ፡ እምነቴ ፡ ሲደክም
የቀደመዉ ፡ ፍቅሬ ፡ ጠፍቶ ፡ ዉስጤ ፡ ሲፍገመገም
አይኔን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ሳነሳ ፡ በፍቅር ፡ እያየኝ
እጄን ፡ ይዞ ፡ አበረታኝ ፡ እንደገና ፡ አቆመኝ

አዝ፦ ልጁ ነኝ ፡ የሚወደኝ ፡ ሚረዳኝ ፡ ሚደግፈኝ
አልሄደም ፡ ካጠገቤ ፡ ፍቅር ፡ ነዉ ፡ ሁሌ ፡ ለእኔ
ኦኦ…..ኦኦኦ…..ልጁ ነኝ………ኦኦኦኦኦ……ልጁ
ነኝ…….ኦኦኦኦኦኦ………ልጁ ነኝ