ከእኔ ፡ ምትፈልገው (Kenie Metfelegew) - ቅድስት ፡ ካሳ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቅድስት ፡ ካሳ
(Kidist Kassa)

Kidist Kassa 1.png


(1)

ተውድጃለሁ
(Tewedejalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2008)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቅድስት ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kidist Kassa)

አዝ፦ ከእኔ ፡ ምትፈልገዉ ፡ የምትሻዉ ፡ ከእኔ
ከእኔ ፡ ምትፈልገዉ ፡ የምትሻዉ ፡ ከእኔ
እንድኖርል ፡ ነዉ ፡ ፍሬ ፡ እንዳፈራ
የተናገርከኝ ፡ ቃል ፡ በሕይወቴ ፡ እንዲሰራ ፡ አባ

ቤትህ ፡ ስመላለስ ፡ ዘመን ፡ እያስቆርጠርኩኝ
ይሄ ፡ ትርጉም ፡ የሌዉ ፡ ዛሬ ፡ ካላደኩኝ
ልጅ ፡ አባቱን ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ እንደ ፡ ማይመስል
መልክህ ፡ ይታይብኝ ፡ ልኑር ፡ እንደቃልህ

አዝ፦ ከእኔ ፡ ምትፈልገዉ ፡ የምትሻዉ ፡ ከእኔ
ከእኔ ፡ ምትፈልገዉ ፡ የምትሻዉ ፡ ከእኔ
እንድኖርል ፡ ነዉ ፡ ፍሬ ፡ እንዳፈራ
የተናገርከኝ ፡ ቃል ፡ በሕይወቴ ፡ እንዲሰራ ፡ አባ
     
አፌ ፡ እያከበረህ ፡ ልቤ ፡ ርቆ ፡ ካንተ
ኑሮዬ ፡ ተግባሬ ፡ አይገልጽህም ፡ አንተን
መልካም ፡ ፍሬ ፡ ላፍራ ፡ ሕይወቴ ፡ ያክብርህ
በመንገድህ ፡ ሊሂድ ፡ አንተን ፡ ልከተልህ

አዝ፦ ከእኔ ፡ ምትፈልገዉ ፡ የምትሻዉ ፡ ከእኔ
ከእኔ ፡ ምትፈልገዉ ፡ የምትሻዉ ፡ ከእኔ
እንድኖርል ፡ ነዉ ፡ ፍሬ ፡ እንዳፈራ
የተናገርከኝ ፡ ቃል ፡ በሕይወቴ ፡ እንዲሰራ ፡ አባ

የልብህ ፡ ምኞትህ ፡ ያንተ ፡ ፍላጎት
ቃልህን ፡ ሰምቼ ፡ እንድኖርበት
መዉደዴ ፡ በስራ ፡ ይሁን ፡ በተግባር
ይህ ነዉ ፡ ያንተ ፡ ደስታ ፡ አንተን ፡ ሳስከብርህ

አዝ፦ ከእኔ ፡ ምትፈልገዉ ፡ የምትሻዉ ፡ ከእኔ
ከእኔ ፡ ምትፈልገዉ ፡ የምትሻዉ ፡ ከእኔ
እንድኖርል ፡ ነዉ ፡ ፍሬ ፡ እንዳፈራ
የተናገርከኝ ፡ ቃል ፡ በሕይወቴ ፡ እንዲሰራ ፡ አባ

የምለምንህ ፡ የምጠይቅህ ፡ ላንተ ፡ እንድኖርልህ
አቅምን ፡ ስጠኝ ፡ እርሱ ፡ ነዉ ፡ የኒለዉጠኝ
የምለምንህ ፡ የምጠይቅህ ፡ ላንተ ፡ እንድኖርልህ
አቅምን ፡ ስጠኝ ፡ እርሱ ፡ ነዉ ፡ የኒለዉጠኝ