From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ባወዳድስ ፡ ባሞጋግስህ ፡ ዝምብዬ ፡ አይደል ፡ አለኝ ፡ ምክንያት
ሁሌ ፡ ይደንቀኛል ፡ ፍቅሩ ፡ ምሕረቱ ፡ ፍጥረት ፡ ይዘምር ፡ ይስገድ ፡ በፊቱ
ኃጥያተኛ ፡ ነሽ ፡ ብለዉ ፡ ፈረጁ
ድንጋይ ፡ አነሱ ፡ ወግረዉ ፡ ሊገድሉኝ
ፈራጁ ፡ እየሱስ ፡ ፈረደልኝ
ደግመሽ ፡ አትስሪ ፡ ሂጅ ፡ አለኝ
ለተመለሰ ፡ ያለፈዉን ፡ ትቶ
ፍርዱ ፍቅር ነዉ ያነሳል ፡ መልሶ
ለተመለሰ ፡ ያለፈዉን ፡ ትቶ
ፍርዱ ፡ ፍቅር ፡ ነዉ ፡ ያነሳል ፡ መልሶ
አዝ፦ ባወዳድስ ፡ ባሞጋግስህ ፡ ዝምብዬ ፡ አይደል ፡ አለኝ ፡ ምክንያት
ሁሌ ፡ ይደንቀኛል ፡ ፍቅሩ ፡ ምሕረቱ ፡ ፍጥረት ፡ ይዘምር ፡ ይስገድ ፡ በፊቱ
ከቤቱ ፡ ጠፋዉ ፡ ድርሻዬን ፡ ይዤ
ተታሎ ፡ ልቤ ፡ በዓም ፡ ተይዤ ፡ ስቃይ
ሆነብኝ ፡ ስቃይ ፡ ሞት ፡ ከበበኝ
ቀኑም ፡ ሌሊቱም ፡ ጨለመብኝ
ልቤን ፡ መልሸየ ፡ እቤቱ ፡ ስገባ
ድግስ ፡ ደግሶ ፡ ተቀበለኝ ፡ አባ
ልቤን ፡ መልሸየ ፡ እቤቱ ፡ ስገባ
ድግስ ፡ ደግሶ ፡ ተቀበለኝ ፡ አባ
አዝ፦ ባወዳድስ ፡ ባሞጋግስህ ፡ ዝምብዬ ፡ አይደል ፡ አለኝ ፡ ምክንያት
ሁሌ ፡ ይደንቀኛል ፡ ፍቅሩ ፡ ምሕረቱ ፡ ፍጥረት ፡ ይዘምር ፡ ይስገድ ፡ በፊቱ
ሳዝን ፡ ስጨነቅ ፡ ዉስጤ ፡ ሲከፋ
መስቀሉን ፡ ሳየዉ ፡ አገኘዉ ፡ ተስፋ
ያባብለኛል ፡ ልጄ ፡ እያለ
በቃሉ ፡ እያዘለለ
እንዳልረበሽ ፡ ዉስጤም ፡ እንዳይፈራ
ያሳድረኛል ፡ በክንፎቹ ፡ ጥላ
እንዳልረበሽ ፡ ዉስጤም ፡ እንዳይፈራ
ያሳድረኛል ፡ በክንፎቹ ፡ ጥላ
አዝ፦ ባወዳድስ ፡ ባሞጋግስህ ፡ ዝምብዬ ፡ አይደል ፡ አለኝ ፡ ምክንያት
ሁሌ ፡ ይደንቀኛል ፡ ፍቅሩ ፡ ምሕረቱ ፡ ፍጥረት ፡ ይዘምር ፡ ይስገድ ፡ በፊቱ
|