አምጡ ፡ በገና (Amtu Begena) - ቅድስት ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቅድስት ፡ ካሳ
(Kidist Kassa)

Kidist Kassa 1.png


(1)

ተውድጃለሁ
(Tewedejalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2008)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:51
ጸሐፊ (Writer): ታምራት ክፍሌ
(Tamrat kifle
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቅድስት ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kidist Kassa)

አዝ፡-አምጡ ፡ በገና ፡ ምክንያት ፡ አለኝ ፡ ለመደርደር
መዳኔ ፡ ብቻ ፡ በቂ ፡ ነዉ ፡ ለእኔ ፡ ለመዘመር (፪x)

አረሳዉም ፡ እኔ ፡ ያኔ ፡ ለእኔ ፡ የሞተዉ ፡ ስለ ፡ እኔ
እንደዉ ፡ ቀላል ፡ አይደል ፡ ይሄ ፡ ሚስጥር ፡ የዳንኩበት ፡ ቀኔ
ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ደስታ ፡ የለም ፡ ለእኔ ፡ ልጁ ፡ የመሆኔ
ድስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ይሄን ፡ ሳስብ ፡ በቂ ፡ ነዉ ፡ መዳኔ

ተነሺ ፡ ይለኛል ፡ ለጌታ ፡ ዘምሪ ፡ ያደረገልሽን
ማዳኑን ፡ አዉሪ ፡ ከበሮ ፡ ይመታ ፡ በገናዉ
ይደርደር ፡ ምስጋዉን ፡ አምጡ ፡ ለስሙ ፡ ይዘመር
እንደ ፡ እኔ ፡ ያሉ ፡ ይዘምሩ
ከሞት ፡ የዳኑ ፡ ይዘምሩ
ለምስጋና ፡ ኑ ፡ ይዘምሩ
ለእርሱ ፡ ዘምሩ ፡ ይዘምሩ (፪x)

አዝ፡-አምጡ ፡ በገና ፡ ምክንያት ፡ አለኝ ፡ ለመደርደር
መዳኔ ፡ ብቻ ፡ በቂ ፡ ነዉ ፡ ለእኔ ፡ ለመዘመር (፪x)

ሰላሜን ፡ ሊያጠፋ ፡ ሊሰርቀኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቢዞርም
ዉስጤ ፡ ተደላድሏል ፡ ተደግፎ ፡ በእግዚአብሔር
የሚታየዉ ፡ ነገር ፡ የሚሰማዉ ፡ አይደል ፡ ማስረጃዬ
እንደ ፡ ወንዝ ፡ የሚፈስ ፡ ደስታ ፡ አለኝ ፡ ይምስገን ፡ ጌታዬ

ተነሺ ፡ ይለኛል ፡ ለጌታ ፡ ዘምሪ ፡ ያደረገልሽን
ማዳኑን ፡ አዉሪ ፡ ከበሮ ፡ ይመታ ፡ በገናዉ
ይደርደር ፡ ምስጋዉን ፡ አምጡ ፡ ለስሙ ፡ ይዘመር
እንደ ፡ እኔ ፡ ያሉ ፡ ይዘምሩ
ከሞት ፡ የዳኑ ፡ ይዘምሩ
ለምስጋና ፡ ኑ ፡ ይዘምሩ
ለእርሱ ፡ ዘምሩ ፡ ይዘምሩ (፪x)