ልጅ ፡ ሰጥተኸኛል (Lej Setehegnal) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 5.jpeg


(5)

ቀሰቀሰኝ ፡ ፍቅርህ
(Qeseqesegn Feqreh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

ልጆች ፡ የእግዚአብሔር ፡ ስጦታዎች ፡ ናቸው [1]
በጐ ፡ ስጦታና ፡ ፍፁም ፡ በረከት
ከላይ ፡ ከብርሃናት ፡ አባት ፡ ዘንድ ፡ ይወርዳሉ [2]

አዝ፦ ልጅ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ አባት ፡ ልታደርገኝ
የራስህን ፡ ፍቅር ፡ ልታስተምረኝ
ገባኝ ፡ ነገሩ ፡ ውሎ ፡ ሳያድር
ቀላል ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ ታላቅ ፡ ሚስጥር

የአምላክ ፡ ስጦታ ፡ ልዩ ፡ በረከት
በእናት ፡ ሆድ ፡ ተዋህዶ ፡ አጥንትና ፡ አጥንት
ከሰው ፡ ሰው ፡ ስትፈጥር ፡ አንተ ፡ ለአንተ ፡ ክብር
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ያሰኘኛል ፡ ተዓምር

አዝ፦ ልጅ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ አባት ፡ ልታደርገኝ
የራስህን ፡ ፍቅር ፡ ልታስተምረኝ
ገባኝ ፡ ነገሩ ፡ ውሎ ፡ ሳያድር
ቀላል ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ ታላቅ ፡ ሚስጥር

ተቀብያለሁ ፡ የእኔን ፡ ስጦታ
የሰጠኸኝን ፡ በረከት ፡ ጌታ
እንደ ፡ ወደድከኝ ፡ አየወደድኩህ
ቤትህ ፡ እኖራለሁ ፡ እያመለኩህ

እግዚአብሔር ፡ ያያል ፡ ጸሎቴን ፡ ይሰማል
በባዕድ ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ ፍሬያማ ፡ ያደርጋል
በጐ ፡ ስጦታና ፡ ፍፁም ፡ በረከት
ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ለእኔ ፡ ሆኗል ፡ የእኔ ፡ አባት

አዝ፦ ልጅ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ አባት ፡ ልታደርገኝ
የራስህን ፡ ፍቅር ፡ ልታስተምረኝ
ገባኝ ፡ ነገሩ ፡ ውሎ ፡ ሳያድር
ቀላል ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ ታላቅ ፡ ሚስጥር

ተቀብያለሁ ፡ የእኔን ፡ ስጦታ
የሰጠኸኝን ፡ በረከት ፡ ጌታ
እንደ ፡ ወደድከኝ ፡ አየወደድኩህ
ቤትህ ፡ እኖራለሁ ፡ እያመለኩህ

  1. መዝሙር ፲፳፮ ፡ ፫ (Genesis 126:3)
  2. የያዕቆብ ፡ መልእክት ፩ ፡ ፲፯ (Genesis 1:17)