From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እንውጣ ፡ ሜዳ ፡ ላይ ፡ አንጨዋወት
ወንድማማቾች ፡ ነን ፡ የአንድ ፡ እናት ፡ አባት
አባብሎ ፡ አባብሎ ፡ ይዞ ፡ አወጣና
ወንድሙን ፡ ገደለው ፡ ቃየል ፡ ጨከነና [1]
የገርማል ፡ ይገርማል
የዘንድሮ ፡ ቃየል ፡ ሲችልበት ፡ ማስመሰል (፪x)
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁኝ ፡ ፈራሁኝ ፡ ለእራሴ
ከእንዲህ ፡ ዓይነቱ ፡ ሰው ፡ ጠብቀኝ ፡ ኢየሱሴ
እንዴት ፡ ተሳካለት ፡ እንዴት ፡ ጥሶ ፡ ወጣ
እንዴት ፡ አሸተተው ፡ መሷዕቱን ፡ ጌታ
ብሎ ፡ የሚቆታ ፡ ሰው ፡ ከገጠማችሁ
ኋላ ፡ ነፍስ ፡ ያተፋል ፡ መልሱት ፡ ባካችሁ
መልሱት ፡ ባካችሁ ፡ ምከርቱት ፡ ባካችሁ (፪x)
ክፉ ፡ ቀን ፡ አለ ፡ ደግ ፡ ቀን ፡ አለ
ባንተዛዘል ፡ እስኪ ፡ ምን ፡ አለ
ጠባቂ ፡ እንሁን ፡ ለወንድማችን
አይቀርምና ፡ መጸጸታችን
እኔማ ፡ ቃልህ ፡ ይሻለናል
እኔማ ፡ የሚል ፡ ና ፡ ተመለስ
እኔማ ፡ ሕይወት ፡ ይሻለኛል
እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ለመንገሥ
እኔማ ፡ ሕይወት ፡ ይሻለኛል
እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ለመንገሥ
|
- ↑ ዘፍጥረት ፬ ፡ ፩ - ፰ (Genesis 4:1-8)