Kefa Mideksa/Hulum Yesma/Hulum Yesma
< Kefa Mideksa | Hulum Yesma
ዘማሪ ኬፋ ሚደቅሳ
አልበም ሁሉም ይስማ
አዝ
አንተ እንደ ረዳኸኝ
አንተ እንዳነሳኸኝ
ሁሉ ይስማ ይወቅልኝ
ሁሉ ይስማ ያመስግንልኝ
ሁሉ ይስማ ይወቅልኝ
ሁሉ ይስማ ያመስግንልኝ (፪x)
ምደረ በዳውን አቋርጫለሁ እጄን ይዘኸኝ ኢየሱስ በሕይወት ኖሪያለሁ አልነደፈኝም እባቡ ጊንጡ አቤት ኢየሱስ በአንተ ተረፍኩ ከስንቱ (፪x) አቤት አባቴ በአንተ ተረፍኩ ከስንቱ
ሲጨላልም የማይነጋ ሲመስል የቅርብ የሩቅ ገለል ገለል ሲል በውድቅቱ ሌሊቱ መጣህና በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንክና
አዘመርከኝ (፫x) እንዳዳንኩህ እንዳገዝኩህ መስክር አልከኝ አባት ሆንከኝ ክብር ሆንከኝ ተሸከምከኝ በደግ እጅህ እቅፍ አርገህ አነሳኸኝ
በምህረትህ ብዛት ቤት አግብተኸኛል አሃሃ (፪x) ቤት አግብተኸኛል በፊትህ ቃል ደስታ ለእኔ ሰጥተኸኛል አሃሃ (፪x) ለእኔ ሰጥተኸኛል ደግሜ ደግሜ የማመሰግንህ ምክኒያቴ ብዙ ነው አሃሃ (፪x) ምክኒያቴ ብዙ ነው ከዛ ከጨካኙ ነፍሴን ከሚፈልግ ከአውሬ አስጥለኸኝ ነው አሃሃ (፪x) ከአውሬ አስጥለኸኝ ነው
አዝ አንተ እንደ ረዳኸኝ አንተ እንዳነሳኸኝ ሁሉ ይስማ ይወቅልኝ ሁሉ ይስማ ያመስግንልኝ ሁሉ ይስማ ይወቅልኝ ሁሉ ይስማ ያመስግንልኝ (፪x)