በል ፡ ተቀበለኝ (Bel Teqebelegn) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 6.jpg


(6)

ሁሉም ፡ ይስማ
(Hulum Yesma)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 3:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

አዝ፦ በል ፡ ተቀበለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቻለሁ
መንገዴ ፡ በዝቶብኝ ፡ ደክሜያለሁ
ምሕረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በእውነት ፡ ይሻላልና
ማረኝ ፡ ልበልህ ፡ አባ ፡ እንደገና

ላይሞላልኝ ፡ ላይሳካልኝ
ከእቅፍህ ፡ ምን ፡ አወጣኝ
ለውድቀቴ ፡ ምክንያቱን ፡ ደርድሬ
ይቆጨኛል ፡ ሳስበው ፡ ዛሬ

አዝ፦ በል ፡ ተቀበለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቻለሁ
መንገዴ ፡ በዝቶብኝ ፡ ደክሜያለሁ
ምሕረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በእውነት ፡ ይሻላልና
ማረኝ ፡ ልበልህ ፡ አባ ፡ እንደገና

በሚመለስ ፡ ደስ ፡ ይልሃልና
ፊትህ ፡ መጣሁ ፡ ይኸው ፡ እንደገና
ክብር ፡ የለም ፡ ውርደት ፡ ነው ፡ ዓለም ፡ ያለው
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መኖር ፡ ሰላም ፡ ነው

አዝ፦ በል ፡ ተቀበለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቻለሁ
መንገዴ ፡ በዝቶብኝ ፡ ደክሜያለሁ
ምሕረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በእውነት ፡ ይሻላልና
ማረኝ ፡ ልበልህ ፡ አባ ፡ እንደገና

ከህልውናህ ፡ ሚሻል ፡ ምን ፡ አለና
መገኘትህ ፡ በቂ ፡ ነውና
እህል ፡ ውኃ ፡ ሞልቶ ፡ ሳይጐለኝ
ክብርህ ፡ ጌታ ፡ ውስጤን ፡ ራበኝ

አዝ፦ በል ፡ ተቀበለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቻለሁ
መንገዴ ፡ በዝቶብኝ ፡ ደክሜያለሁ
ምሕረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በእውነት ፡ ይሻላልና
ማረኝ ፡ ልበልህ ፡ አባ ፡ እንደገና