የሚያውቅልኝ ፡ ጌታ (Yemiyawqelegn Gieta) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 3.jpg


(3)

ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
(Hulu Beju New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

የሚያውቅልኝ ፡ ጌታ ፡ ያውቅልኛልና
ሰው ፡ አልደገፍም ፡ ይሰበራልና
ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ነገ ፡ በሚጠፋው ፡ ነገር
ልቤን ፡ በዚያ ፡ አልጥልም ፡ አለልኝ ፡ እግዚአብሔር (፪x)

አለልኝ ፡ እግዚአብሔር (፬x)
አለልኝ ፡ አለልኝ ፡ የሚያስብልኝ (፪x)

የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ በላይ
እኩያ ፡ የሌለህ ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x)

አምላክ ፡ አለኝና ፡ ሁሉን ፡ በእጁ ፡ የያዘ
ሥሙም ፡ ድንቅ ፡ መካር ፡ ኃያል ፡ የተባለ
ሰማይና ፡ ምድርን ፡ በቃሉ ፡ እንዳፀና
እርሱን ፡ ባይሁ ፡ ጊዜ ፡ እኔም ፡ ልቤ ፡ ፀና (፭x)

ግራ ፡ አይገባኝም ፡ ነገን ፡ አስቤ ፡ ለወደፊቱ
የታመንኩበት ፡ ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ በደጁ
የእንቆቅልሽ ፡ ሁሉ ፡ መፍቻ ፡ ቁልፍ ፡ ያለው
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው

እንዳለው ፡ ነው ፡ እንደ ፡ ቃሉ
ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ሁሉ ፡ በደጁ
እንዳለው ፡ ነው ፡ (እንዳለው ፡ ነው)
እንደ ፡ ቃሉ ፡ (እንደ ፡ ቃሉ)
ሁሉ ፡ በእጁ ፡ (ሁሉ ፡ በእጁ)
ሁሉ ፡ በደጁ ፡ (ሁሉ ፡ በደጁ) (፪x)

የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ በላይ
እኩያ ፡ የሌለህ ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x)