ተዓምር ፡ ነው (Teamer New) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 3.jpg


(3)

ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
(Hulu Beju New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

ስለደህንነቴ/ስለመጠራቴ ፡ ዘምሬ ፡ ሳልጨርስ
ወደ ፡ ሌላ ፡ አላልፍም ፡ ጐርፍ ፡ . (1) . ፡ ቢደርስ
በክብር ፡ ወደላይ ፡ ያረገውን ፡ ንጉሥ
ደስታዬ ፡ ልክ ፡ የለው ፡ እርሱን ፡ ሳሞጋግስ (፪x)

እርሱን ፡ ሳሞጋግስ (፪x) ፣ ጌታን ፡ ሳሞጋግስ (፪x)
እርሱን ፡ ሳሞጋግስ (፪x) ፣ ጌታን ፡ ሳሞጋግስ (፪x)

በምሥጋና ፡ ልቁም ፡ ፊቱ ፡ በደስታ (፪x)
እግሮቼም ፡ ጸኑልኝ ፡ ቆምኩኝ ፡ በከፍታ (፪x)
መዳኔ ፡ ማምለጤ ፡ ኦሆሆ ፡ ትንግርት ፡ ሆኖብኛል (፪x)
በሚወደው ፡ ልጁ ፡ እግዚአብሔር/ጌታዬ ፡ ታርቆኛል (፪x)

አዝ፦ ተዓምር ፡ ነው ፡ መዳኔ ፡ ለእኔ
ቆሜ ፡ ፊትህ ፡ መዘመሬ
ወደኸኝ ፡ ድኛለሁና
ተቀበል ፡ ከእኔ ፡ ምሥጋና

ከእኔ ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፤ ከእኔ ፡ ምሥጋና
ከእኔ ፡ አምልኮ ፤ ከእኔ ፡ አምልኮ
ከእኔ ፡ ዝማሬ ፤ ከእኔ ፡ ዝማሬ
ከእኔ ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፤ ከእኔ ፡ ምሥጋና

እኔስ ፡ ከነገሬ ፡ ድኜ ፡ መዘመሬ (፪x)
ከሁሉም ፡ ሚበልጠው ፡ መዳኔ ፡ ነው ፡ ክብሬ (፪x)
ሰው ፡ ሆነህ ፡ ከሰማይ ፡ የወረድከው ፡ ጌታ (፪x)
ሁሌ ፡ ላመስግንህ ፡ አለብኝ ፡ ውለታ (፪x)

አዝ፦ ተዓምር ፡ ነው ፡ መዳኔ ፡ ለእኔ
ቆሜ ፡ ፊትህ ፡ መዘመሬ
ወደኸኝ ፡ ድኛለሁና
ተቀበል ፡ ከእኔ ፡ ምሥጋና

ከእኔ ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፤ ከእኔ ፡ ምሥጋና
ከእኔ ፡ አምልኮ ፤ ከእኔ ፡ አምልኮ
ከእኔ ፡ ዝማሬ ፤ ከእኔ ፡ ዝማሬ
ከእኔ ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፤ ከእኔ ፡ ምሥጋና