ስላሰብከኝ (Selasebkegn) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 3.jpg

(3)

ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
(Hulu Beju New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

እንደነጋልኝ ፡ አይቶ ፡ ጠላቴ
ከበሮውን ፡ ጥሎ ፡ ሮጠ ፡ ከፊቴ
ድሌን ፡ ለማየት ፡ አልቻለምና
ተራመድኩበት ፡ ነጋልኝና (፪x)

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በአንድ ፡ ቀን ፡ ጀንበር ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራኸው
ስላሰብከኝ ፡ ስለወደደከኝ ፡ ነው ፡ በቤትህ ፡ የቆምኩት
ነግቶልኝ ፡ ነው ፡ በጉባኤ ፡ መሃል ፡ ለአንተ ፡ የዘመርኩት (፪x)

ሚታመኑህን ፡ የምታኮራ
ያልተጠበቀን ፡ ድንቅ ፡ የምትሰራ
አይቼሃለሁ ፡ ስትታደገኝ
ከጠላቴ ፡ ቀስት ፡ ስታስመልጠኝ (፪x)

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በአንድ ፡ ቀን ፡ ጀንበር ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራኸው
ስላሰብከኝ ፡ ስለወደደከኝ ፡ ነው ፡ በቤትህ ፡ የቆምኩት
ነግቶልኝ ፡ ነው ፡ በጉባኤ ፡ መሃል ፡ ለአንተ ፡ የዘመርኩት (፪x)

በጠዋት ፡ ማታ ፡ ጠብቀኸኛል
ከጐኔ ፡ አለህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
ጽኑ ፡ ግንቤ ፡ ነህ ፡ በጠላቴ ፡ ፊት
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሆኜ ፡ አላውቅም ፡ ሽንፈት (፪x)

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በአንድ ፡ ቀን ፡ ጀንበር ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራኸው
ስላሰብከኝ ፡ ስለወደደከኝ ፡ ነው ፡ በቤትህ ፡ የቆምኩት
ነግቶልኝ ፡ ነው ፡ በጉባኤ ፡ መሃል ፡ ለአንተ ፡ የዘመርኩት (፪x)