ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (Qedus Egziabhier) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 3.jpg


(3)

ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
(Hulu Beju New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የነበርከው
አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ከለላ ፡ የሆንከው (፬x)

ሌላማ ፡ ምን ፡ እከፍልሃለሁ
ምሥጋና ፡ በፊትህ ፡ እሰዋለሁ (፪x)

አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ያደረከኝ
ከዚያ ፡ ከጨለማ ፡ ከሞት ፡ የታደከኝ
ስለ ፡ እኔ ፡ የቆሰልከው ፡ የደቀቀከው ፡ ጌታ
በልቤ ፡ ይኖራል ፡ የአንተ ፡ ውለታ (፪x)

ይገርመኛል ፡ ከሞት ፡ መትረፌ
ይገርመኛል ፡ በአንተ ፡ መታቀፌ
ይገርመኛል ፡ ቸሩ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይገርመኛል ፡ ሆንክልኝ ፡ መከታ (፫x)

በረሃብ ፡ ዘመን ፡ ጥጋብ ፡ ሲሆንልኝ ፡ ያዩ
ዛሬ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አንተን ፡ ያመልካሉ
እኔም ፡ በመደነቅ ፡ በመገረም ፡ ሆኜ
አመልክሃለሁኝ ፡ በመቅደስህ ፡ ቆሜ (፪x)

ይገርመኛል ፡ ከሞት ፡ መትረፌ
ይገርመኛል ፡ በአንተ ፡ መታቀፌ
ይገርመኛል ፡ ቸሩ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይገርመኛል ፡ ሆንክልኝ ፡ መከታ (፫x)