From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ምክርህ ፡ ሲሰራ ፡ አይቼ ፡ ተደስቻለሁ
ማይከለከል ፡ ሃሳብህ ፡ አውቄዋለሁ
ድንቅህን ፡ አይቼ ፡ ብገረም ፡ ቆምኩኝ ፡ ላመልክህ
በሰው ፡ ሁሉ ፡ ፊት ፡ ተገልጧል ፡ አደራረግህ
አዝ፦ ተባረክ ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አውቄያለሁ
ዘመኔን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንድኖር ፡ ጌታ
በቃልህ/በምክርህ ፡ ደገፍከኝ ፡ እንዳልረታ (፪x)
አንተን ፡ አምኜ ፡ ወደፊት ፡ እራመዳለሁ
ወሬ ፡ ሰምቼ ፡ ኋላዬን ፡ መቼ ፡ አያለሁ
ዘለዓለሜ ፡ በእጅህ ፡ ነው ፡ ልቤ ፡ እንዳይሰጋ
የምታመንህ ፡ ጌታዬ ፡ አለህ ፡ ከእኔ ፡ ጋር
አዝ፦ ተባረክ ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አውቄያለሁ
ዘመኔን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንድኖር ፡ ጌታ
በቃልህ/በምክርህ ፡ ደገፍከኝ ፡ እንዳልረታ (፪x)
የሰው ፡ ዓይን ፡ የለህ ፡ እንደሰው ፡ መቼ ፡ ታያለህ
ጆሮህስ ፡ እንደሰማቸው ፡ መች ፡ ትፈርዳለህ
መንገዱ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ሚመራህ ፡ የለም
በምክርህ ፡ ግሩም ፡ ትክክል ፡ ጻድቅ ፡ አምላክ ፡ ነህ
አዝ፦ ተባረክ ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አውቄያለሁ
ዘመኔን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንድኖር ፡ ጌታ
በቃልህ/በምክርህ ፡ ደገፍከኝ ፡ እንዳልረታ (፪x)
ለዘሪ ፡ ዘርን ፡ የምትሰጥ ፡ ፍሬ ፡ እንዲበላ
ከሕይወት ፡ እንዳይጐድል ፡ ሞቶ ፡ የኋላ ፡ ኋላ
ለእኔም ፡ ቃልህን ፡ ሰጥተኸኛል ፡ ምን ፡ አስባለሁ
ተስፋ ፡ ቢስ ፡ ሆኜ ፡ አልቀረሁም ፡ አከብርሃለሁ
አዝ፦ ተባረክ ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አውቄያለሁ
ዘመኔን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንድኖር ፡ ጌታ
በቃልህ/በምክርህ ፡ ደገፍከኝ ፡ እንዳልረታ (፪x)
|