ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታ (Eyesus New Gieta) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 3.jpg


(3)

ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
(Hulu Beju New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

አምልኮ (፫x) ፡ ይለኛል
ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ መንፈስህ ፡ በእጥፍ ፡ አግኝቶኛል
በል ፡ ዘምር (፫x) ፡ ይለኛል
የሚወደኝ ፡ ጌታ ፡ ምህረት ፡ አድርጐልኛል

ጠላት ፡ በዙሪያዬ ፡ መርዶ ፡ ሲያረዳኝ
የጌታዬ ፡ ሰላም ፡ ከላይ ፡ ሲያገኘኝ
አስባለኝ ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፪x)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ አሃ ፡ አለሁ ፡ የሚል ፡ ጠፍቶ
ጀግና ፡ የተባል ፡ አሃ ፡ ሁሉ ፡ አንገቱን ፡ ደፍቶ
መጽሐፉን ፡ ወስዶ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታ

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x)
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታ (፪x)

ከአንተ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ንጉሥ
በላዬ ፡ አልሾምኩም ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥም ፡ ያለህ ፡ አንተ ፡ ነህ
በፍጥረት ፡ አንደበት ፡ ትመሰገናለህ

ጌታዬ ፡ ትመሰገናለህ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ ትመሰገናለህ (፪x)

አልቅነትና ፡ ሥልጣናትን ፡ ገፎ
በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ አለ ፡ ሁሉን ፡ አሸንፎ
የሁሉ ፡ የበላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚገዛው
እኔ ፡ የማመልከው ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው

ኢየሱስ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው (፬x)

አምልኮ (፫x) ፡ ይለኛል
ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ መንፈስህ ፡ በእጥፍ ፡ አግኝቶኛል
በል ፡ ዘምር (፫x) ፡ ይለኛል
የሚወደኝ ፡ ጌታ ፡ ምህረት ፡ አድርጐልኛል

ጠላት ፡ በዙሪያዬ ፡ መርዶ ፡ ሲያረዳኝ
የጌታዬ ፡ ሰላም ፡ ከላይ ፡ ሲያገኘኝ
አስባለኝ ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፪x)