በቃ ፡ ብሎ (Beqa Belo) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 3.jpg


(3)

ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
(Hulu Beju New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

አዝ፦ ሆኖልኛል ፡ ቀን ፡ ሆኖልኛል ፡ ደስ ፡ ብሎኛል
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቶልኛል (፪x)

ነጋ ፡ ጠባ ፡ ተመስገን ፡ እለዋለሁ
የሞት ፡ ደጃፍ ፡ ተዘግቶ ፡ አይቻለሁ (፪x)

መገረም ፡ ሞልቶኛል ፡ ጌታ ፡ መውደዱ ፡ ገኖ ፡ ሲወጣ
ቆሜ ፡ ከመዘመር ፡ በቀር ፡ ምለውን ፡ አንዳች ፡ እስካጣ
የክብሩ ፡ ጸዳል ፡ ሲያበራ ፡ እኔን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ሲጣራ
ከልካይ ፡ አልነበረም ፡ ፊቱ ፡ ሲበራ ፡ ለእኔ ፡ መብራቱ

አዝ፦ ብሩህ ፡ ቀን ፡ ሆኖልኛል ፡ ደስ ፡ ብሎኛል
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቶልኛል (፪x)

ነጋ ፡ ጠባ ፡ ተመስገን ፡ እለዋለሁ (እለዋለሁ)
የሞት ፡ ደጃፍ ፡ ተዘግቶ ፡ አይቻለሁ (በዓይኔ) (፪x)

ዓይነጋም ፡ ብሎ ፡ ንጋቴን ፡ ሲረግምብኝ ፡ ሰማሁና
እኔም ፡ ጠላት ፡ ያለውን ፡ ለአምላኬ ፡ ተናገርኩና
ቀን ፡ አለው ፡ አምላኬ ፡ ከላይ ፡ በዓይኖቹ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሲያይ
ጠላት ፡ መግቢያውን ፡ አጣ ፡ ዓይኔ ፡ አያየው ፡ ተቀጣ

አዝ፦ ብሩህ ፡ ቀን ፡ ሆኖልኛል ፡ ደስ ፡ ብሎኛል
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቶልኛል (፪x)

ነጋ ፡ ጠባ ፡ ተመስገን ፡ እለዋለሁ (እለዋለሁ)
የሞት ፡ ደጃፍ ፡ ተዘግቶ ፡ አይቻለሁ (በዓይኔ) (፪x)

በቃ ፡ ብሎ ፡ ገስጾ ፡ ወጀቡን ፡ ለእኔ ፡ አዞ
አሳለፈኝ ፡ ጌታዬ ፡ ላክብረው ፡ በዜማዬ (፪x)
ላክብረው ፡ በዜማዬ (፬x) ፤ ላክብረው ፡ በተራዬ (፬x)