በለቅሶ ፡ ፈንታ (Beleqso Fenta) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 3.jpg


(3)

ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
(Hulu Beju New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

በለቅሶ ፡ ፈንታ ፡ ደስታ
በሃዘን ፡ ምትክ ፡ እፎያታ
አደረገልኝ ፡ አምላኬ
አመልከዋለሁ ፡ ከልቤ
አመልከዋለሁ ፡ ከልቤ (፬x)

የገባሁበት ፡ ገብቶ ፡ ጌታዬ ፡ እኔን ፡ ረድቶ (፪x)
አይቻለሁኝ ፡ በዓይኔ ፡ ታሪኬ ፡ ተለውጦ
የገባሁበት ፡ ገብቶ ፡ ጌታዬ ፡ እኔን ፡ ረድቶ (፪x)
አይቻለሁኝ ፡ በዓይኔ ፡ ታሪኬ ፡ ተለውጦ

ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር
ስላረክልኝ ፡ ነገር
ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር
ከማመስገን ፡ በቀር (፪x)

በምድረበዳ ፡ መራኝ ፡ ከእጆቹ ፡ እያበላኝ (፪x)
ከአበልኝ ፡ በጐነት ፡ አንዳችም ፡ ሳያሳጣኝ (፪x)
በምድረበዳ ፡ መራኝ ፡ ከእጆቹ ፡ እያበላኝ (፪x)
ከአበልኝ ፡ በጐነት ፡ አንዳችም ፡ ሳያሳጣኝ (፪x)

ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር
ስላረክልኝ ፡ ነገር
ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር
ከማመስገን ፡ በቀር (፪x)

በቸርነቱ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ
ስለወደደ ፡ ነው ፡ ወግ ፡ ማረግ ፡ ያሳየኝ
በቸርነቱ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ
ስለወደደ ፡ ነው ፡ ወግ ፡ ማረግ ፡ ያሳየኝ

ተባረክ ፡ ብዬ ፡ አልረካሁም ፡ ጌታዬ (፪x) ፡ ባለውለታዬ
ከፍ ፡ በል ፡ ብዬ ፡ አልረካሁም ፡ ጌታዬ (፪x) ፡ ባለውለታዬ
ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ (፰x)