አይረሳኝም (Ayresegnem) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 3.jpg


(3)

ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
(Hulu Beju New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

እኔስ ፡ አልረሳሁም ፡ ያደረክልኝን
ከጨለማ ፡ አውጥተህ ፡ ቀን ፡ ያወጣህልኝ (፪x)
ምስኪኑን ፡ ከጉድፍ ፡ ከአመድ ፡ አንስተኸው
ከታላላቆች ፡ ጋር ፡ ስፍራ ፡ እንደሰጠኸኝ (፪x)

አይረሳኝም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ያረክልኝ ፡ ብዙ ፡ ውለታ
አይረሳኝም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለእኔ ፡ ተንገላታህ
አይረሳኝም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ያረክልኝ ፡ ብዙ ፡ ውለታ
አይረሳኝም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የሆንክልኝ ፡ በጐልጐታ

መቆም ፡ መቀመጤን ፡ በፊትህ ፡ አድርገህ
ክፉ ፡ አንዳይነካኝ ፡ በዙሪያዬ ፡ ሆነህ (፪x)
የአመጽ ፡ ፈሳሽ ፡ አልፎ ፡ ቀን ፡ ወጣልኝ ፡ ለእኔ
ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለመዳኔ (፪x)

የመኖሬ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
የመክበሬ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
የመቆሜ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፬x)

የተቆረጠና ፡ የአለቀውን ፡ ነገሬን
ቀጥለህልኛል ፡ አይተህ ፡ መቸገሬን (፪x)
ብቻህን ፡ ያለአጋዥ ፡ የረዳኸን ፡ ጌታ
ዘምረ ፡ ያሰኘኛል ፡ በዝቶ ፡ የአንተ ፡ ውለታ (፪x)

የመኖሬ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
የመክበሬ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
የመቆሜ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፬x)