Kefa Mideksa/Hulu Beju New/And Wedaj

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ኬፋ ሚደቅሳ ርዕስ አንድ ወዳጅ አልበም ሁሉ በእጁ ነው

አንድ ወዳጅ (፪x) አለኝ ለእኔ የሞተልኝ (፬x)

ቅጣቴን የተቀጣህልኝ አበሳዬን ከእኔ ወሰድክልኝ (፪x) ጌታ ተባረክልኝ ኢየሱስ ተባረክልኝ ጌታ ተባረክልኝ (፪x)

ሙግቴን ተሟግቶ አሸንፎልኛል ጠላቴ እንዳይከሰኝ ነጻ ነህ ብሎኛል ይህን ወዳጄን ወዳጄ ነህ ያልኩት ከማንም አብልጬ በልቤ የሾምኩት

አዝ ለእኔ መልካም በማድረግ የታወቀው መልካም በማድረግ የታወቀው ለእኔ መልካም በማሰብ የታወቀው መልካም በማሰብ የታወቀው እርሱ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው (፪x) እርሱ ጌታዬ ነው ጌታዬ ነው (፪x)

በምክሩ ግሩም ነው ነፍስን ይመልሳል ከወዳጅ አብልጦ ወደ ልብ ይጠጋል ደብቆ የያዘኝ እንዳልሆን የሌላ የቅርቤ የምለው ማነው ከእርሱ ሌላ

አዝ ለእኔ መልካም በማድረግ የታወቀው መልካም በማድረግ የታወቀው ለእኔ መልካም በማሰብ የታወቀው መልካም በማሰብ የታወቀው እርሱ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው (፪x)

እርሱ ጌታዬ ነው ጌታዬ ነው (፪x) እርሱ ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው (፪) እርሱ አባቴ ነው አባቴ ነው (፪) እርሱ ንጉሴ ነው ንጉሴ ነው (፪) እርሱ ወዳጄ ነው ወዳጄ ነው (፪)