አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋር (Ale Kenie Gar) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 3.jpg


(3)

ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
(Hulu Beju New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

በቃልህ ፡ ኖራለሁ ፡ ቃልህን ፡ አምናለሁ (አምናለሁ)
ካሰብክልኝ ፡ ታድያ ፡ ለምን ፡ እሠጋለሁ (ለምን ፡ እሰጋለሁ)
እራሴን ፡ ጠብቄ ፡ ማኖር ፡ ስለማልችል (ስለማልችል)
ተመካሁ ፡ በጌታ ፡ ሁሉን ፡ በምትችል (፪x)

አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ በከፍታ/በደስታ ፡ እኖራለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
የዘላለም ፡ ተድላዬ ፡ በሆንከኝ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ
ጌታ ፡ በእራስህን ፡ ታምነህ ፡ ጠርተኸኝ ፡ አይቻለሁ
ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ ዘምራለሁ (፬x)

እንዴት ፡ እንደረዳኝ ፡ እኔ ፡ አውቃለሁ
እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ እኮ ፡ ልዩ ፡ ነው
እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ እኮ ፡ ልዩ ፡ ነው
እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው
እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ እኮ ፡ ልዩ ፡ ነው

ምህረት ፡ ማይገባኝ ፡ ነበርኩኝ ፡ አውቃለሁ
ለእኔ ፡ ማዘንህን ፡ በአይኔ ፡ አይቻለሁ
ጌታ ፡ በጎነትህ ፡ ለእኔ ፡ ስለበዛ
ብዙ ፡ መሰናክል ፡ አለፍኩ ፡ እንደ ፡ ዋዛ (፪x)

አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ በከፍታ/በደስታ ፡ እኖራለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
የዘላለም ፡ ተድላዬ ፡ በሆንከኝ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ
ጌታ ፡ በራስህን ፡ ታምነህ ፡ ጠርተኸኝ ፡ አይቻለሁ
ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ ዘምራለሁ (፬x)

የማይጠፋ ፡ ተስፋ ፡ የዘላለም ፡ ሕይወት
በአንተ ፡ አግኝቻለሁ ፡ ፍፁሙን ፡ በረከት
በፍቅርህ ፡ መንግስትህ ፡ በደስታ ፡ ኖራለሁ
ሳቅ ፡ አድርገህልኛል ፡ እዘምርልሃለሁ (፪x)

እንዴት ፡ እንደረዳኝ ፡ እኔ ፡ አውቃለሁ
እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ እኮ ፡ ልዩ ፡ ነው
እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ እኮ ፡ ልዩ ፡ ነው
እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው
እኔ ፡ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ እኮ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)