From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ለበጐ ፡ ነው ፡ የሚሆነው ፡ ሁሉ
ተረድቼዋለሁ
የታለ ፡ አትበሉ ፡ ለእኔ ፡ ይታየኛል
ለእኔ ፡ ይታየኛል (፪x)
ያገኘኛል ፡ ያልኩት ፡ በእርግጥ ፡ ያገኘኛል
በእርግጥ ፡ ያገኘኛል (፪x)
የዘገየ ፡ ሲመስል ፡ በጊዘው ፡ ይመጣል
በጊዘው ፡ ይመጣል (፪x)
እንዳሳየኝ ፡ ያው ፡ እንዳለኝ ፡ ይሆናል
እንዳለኝ ፡ ይሆናል (፪x)
አዝ፦ የሚሆነው ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ አውቃለሁ
አምላኬ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላማው ፡ መልካም ፡ ነው (፪x)
(አላማው) አላማው ፡ መልካም ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ መልካም ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ የድል ፡ ነው
የሌለውን ፡ ነገር ፡ እንዳለ ፡ አድርጐ ፡ ይጠራል
እንዳለ ፡ አድርጐ ፡ ይጠራል (፪x)
ለሙታን ፡ ሕይወትን ፡ ጌታዬ ፡ ይሰጣል
ጌታዬ ፡ ይሰጣል (፪x)
አበቃለት ፡ ሲባል ፡ ነገሩ ፡ ሲዘጋ
ነገሩ ፡ ሲዘጋ (፪x)
የሁሉ ፡ መክፈቻ ፡ ቁልፍ ፡ አለ ፡ እርሱ ፡ ጋር
ቁልፍ ፡ አለ ፡ እርሱ ፡ ጋር (፪x)
አዝ፦ የሚሆነው ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ አውቃለሁ
አምላኬ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላማው ፡ መልካም ፡ ነው (፪x)
(አላማው) አላማው ፡ መልካም ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ መልካም ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ የድል ፡ ነው
ማዕበሉ ፡ በዝቶ ፡ ወጀቡ ፡ ቢያይልም
ወጀቡ ፡ ቢያይልም (፪x)
ወደፊት ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ አልልም
ወደ ፡ ኋላ ፡ አልልም (፪x)
በውሃው ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ና ፡ ያለው
ወደ ፡ እኔ ፡ ና ፡ ያለው (፪x)
ሊያሰጥመኝ ፡ አይደለም ፡ እምነት ፡ ሊያሳየኝ ፡ ነው
እምነት ፡ ሊያሳየኝ ፡ ነው
ሊያሸጋግረኝ ፡ ነው
አዝ፦ የሚሆነው ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ አውቃለሁ
አምላኬ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላማው ፡ መልካም ፡ ነው (፪x)
(አላማው) አላማው ፡ መልካም ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ መልካም ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ የድል ፡ ነው
ከልካይ ፡ አይኑርብኝ ፡ ጌታን ፡ ላምልከው
አላማው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ሁሌም ፡ መልካም ፡ ነው
ሁሌም ፡ መልካም ፡ ነው
ጌታ ፡ መልካም ፡ ነው
ከሳሼ ፡ ገለል ፡ በል ፡ ጌታን ፡ ላክብረው
አላማው ፡ በእኔ ፡ እላይ ፡ ሁሌም ፡ መልካም ፡ ነው
ሁሌም ፡ መልካም ፡ ነው
ጌታ ፡ መልካም ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ መልካም ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ መልካም ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው
(አላማው) አላማው ፡ የድል ፡ ነው (፪x)
|