ህልሜ ፡ ሰምሯል (Helmie Semrual) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kasahun Lema)

Kasahun Lema 1.jpg


(1)

እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው
(Egziabhier Qen Alew)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kasahun Lema)

አዝ፦ ህልሜ ፡ ሰምሯል ፡ በልጅነት ፡ ያየሁት
በውሃ ፡ ውስጥ ፡ ያለፍኩለት ፡ በእሳት
አልቀረሁም ፡ እንዳሰበው ፡ ያ ፡ ጠላቴ
ሁሉን ፡ አለፍኩ ፡ አቅም ፡ ሆኖኝ ፡ ቸር ፡ አባቴ (፪x)

ሰምቼ ፡ ድላድ ፡ የነፃነት ፡ ፋና
ከሞት ፡ አምልጫለሁ ፡ ከድቅድቅ ፡ ጨለማ
የአዲስ ፡ ነገር ፡ ጅምር ፡ የታሪክ ፡ ምዕራፍ
ጌታ ፡ ከፍቶልኛል ፡ የበረከት ፡ ደጃፍ

አዝ፦ ህልሜ ፡ ሰምሯል ፡ በልጅነት ፡ ያየሁት
በውሃ ፡ ውስጥ ፡ ያለፍኩለት ፡ በእሳት
አልቀረሁም ፡ እንዳሰበው ፡ ያ ፡ ጠላቴ
ሁሉን ፡ አለፍኩ ፡ አቅም ፡ ሆኖኝ ፡ ቸር ፡ አባቴ (፪x)

በእውነት ፡ የታመንክ ፡ ነህ ፡ ከቃልህ ፡ አንድ ፡ አይወድቅም
ልትሰራ ፡ ተነስተህ ፡ አቅም ፡ አጥተህ ፡ አታውቅም
የተረሳሁ ፡ ሲመስለኝ ፡ ስባል ፡ አስታዋሽ ፡ የለው
አንተ ፡ ስትራራልኝ ፡ አዲስ ፡ ነገርን ፡ አየሁ

ወደኋላ ፡ አልልም ፡ ያየልኝ ፡ አለና
አምላኬ ፡ ከፊቴ ፡ ቀድሞኝ ፡ ወጥቷልና
ልሂድ ፡ ልዘርጋ ፡ እንጂ ፡ ዱሩንም ፡ ልመንጥር
አለ ፡ ካለሁበት ፡ የሚበልጥ ፡ ክብር (፪x)

አዝ፦ ህልሜ ፡ ሰምሯል ፡ በልጅነት ፡ ያየሁት
በውሃ ፡ ውስጥ ፡ ያለፍኩለት ፡ በእሳት
አልቀረሁም ፡ እንዳሰበው ፡ ያ ፡ ጠላቴ
ሁሉን ፡ አለፍኩ ፡ አቅም ፡ ሆኖኝ ፡ ቸር ፡ አባቴ (፪x)