From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በእቅፍህ ፡ መሃል ፡ ስፍራን ፡ ሰጠኸኝ ፡ ተደላድዬ
እፎይ ፡ ብያለሁ ፡ አንተን ፡ አግኝቼ ፡ ክበር ፡ ጌታዬ
እንዳልታወክ ፡ በቀኜ ፡ አለህ ፡ ውስጤ ፡ መች ፡ ሰግቶ
ልቤም ፡ ይጣራል ፡ ኢየሱስ ፡ እያለ ፡ በፍቅርህ ፡ ነዶ (፪x)
አዝ፦ (ኢየሱስ) ፡ የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ (ኢየሱስ) ፡ የሆንክልኝ ፡ ፍቺ (፪x)
(ኢየሱስ) ፡ ክብርን ፡ አይቻለሁ ፡ (ኢየሱስ) ፡ እኔስ ፡ በአንተ ፡ እጅ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ አምላክ ፡ ወረት ፡ የማታውቅ ፡ እሩህሩህ ፡ ጌታ
ፍቅርህ ፡ ማረከኝ ፡ የአንተ ፡ እንድሆን ፡ ልቤም ፡ ተረታ
ሌላ ፡ አይገዛንም ፡ ከአንተ ፡ በስተቀር ፡ በምድር ፡ ያለው
ሁሉ ፡ የሞላህ ፡ ባለ ፡ ፀጋ ፡ አምላክ ፡ አንተን ፡ ይዣለሁ (፪x)
ክበርልኝ (፫x)
አላየሁም ፡ ከአንተ ፡ የሚበልጥብኝ
ንገስልኝ (፫x)
አልሰማሁም ፡ ከአንተ ፡ የሚበልጥብኝ
አላየሁም ፡ ከአንተ ፡ የምበልጥብኝ
አልሰማሁም ፡ ከአንተ ፡ የምበልጥብኝ (፪x)
ስትሾም ፡ ስትሸልም ፡ (አቤት ፡ ስታውቅበት)
ደርሰህ ፡ ብርሃን ፡ (ስትሆን ፡ ቀን ፡ ለጨለመበት)
ስታውቅበት ፡ ማበጃጀት
|