From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ኢየሱስ ፡ አለቴ ፡ ነህ ፡ ተደግፌሃለሁ
አንተ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህ ፡ በጥላህ ፡ አርፋለሁ
ከቶ ፡ አልጨነቅም ፡ ለነገዬ ፡ ብዬ
ሁሉን ፡ የምትሆን ፡ ስላለህ ፡ ጌታዬ
ሁሉን ፡ የምትሆን ፡ ስላለህ ፡ ጌታዬ (፪x)
አዝ፦ እልፍ ፡ ቃል ፡ ቢኖረኝ ፡ አንተን ፡ ማሞገሻ (፪x)
አመስግኜ ፡ አልጠግብም ፡ እስከመጨረሻ (፪x)
ባለ ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ባለ ፡ ብዙ ፡ ፀጋ
ማንስ ፡ ወድቆ ፡ ቀርቷል ፡ አንተን ፡ የተጠጋ
በጊዜው ፡ የምትደርስ ፡ ተቀድመህ ፡ አታውቅም
ታማኝ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትዋሽም
ታማኝ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትዋሽም (፪x)
አዝ፦ እልፍ ፡ ቃል ፡ ቢኖረኝ ፡ አንተን ፡ ማሞገሻ (፪x)
አመስግኜ ፡ አልጠግብም ፡ እስከመጨረሻ (፪x)
ይገርመኛል ፡ ይደንቀኛል
ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ለኔ ፡ ያለህ ፡ አላማ
ፍፁም ፡ ደግነትህ (፪x)
ልትመለክ ፡ የሚገባህ
ልትወደስ ፡ የሚገባህ (፪x)
ገናና ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ የበላይ
ከፍ ፡ በል ፡ በምድርም ፡ በሰማይ (፪x)
ብንሰግድልህ
|