From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ርዕስ እግዚአብሔር ቀን አለው
ዘማሪ ካሳሁን ለማ
አልበም እግዚአብሔር ቀን አለው
ለቅሶ ማታ ቢሆንም ጠዋት ደስታp ይሆናል
ሁሉን ቻዩ ጌታ እግዚአብሔር ቀን ያዛል (፪x)
አዝ
ቢመሽም ይነጋል ይነጋል ይህንን አውቃለሁ
እንደጨለመ አይቀር አይቀርም እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x)
እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉ
እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x)
አልገፋ ብሉ ትላንት ያስቸገረኝ
ከፊቴ እየቆመ አላሳልፍ ያለኝ
ታሪክን በታሪክ በሚሽረው ጌታ
ሁሉ ተለወጠ በቃ ሲል አበቃ (፪x)
አያሳፍር ለተደገፉበት
ይታመናል ተስፋ ላረጉበት
መልካም አምላክ ሁሌም ባለፀጋ
እንደርሱ የለም ፈጥኖ የሚረዳ (፪x)
አዝ
ቢመሽም ይነጋል ይነጋል ይህንን አውቃለሁ
እንደጨለመ አይቀር አይቀርም እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x)
እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉ
እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x)
አንድ ጊዜ ቃሉን ሲሰጥ ሊሰራ ሲነሳ
ነገር ሁሉ ይለወጣል ከእርሱ የተነሳ
እኔም ይሄ ገብቶኝ ተደግፌዋለሁ
በኃያላን መሃል ኃይል የእግዚአብሄር ነው
በኃያላን መሃል ኃይል የእግዚአብሄር ነው (፪x)
ኃይል የእግዚአብሔር ነው (፰x)
ለቅሶ ማታ ቢሆንም ጠዋት ደስታ ይሆናል
ሁሉን ቻዩ ጌታ እግዚአብሔር ቀን ያዛል (፪x)
አዝ
ቢመሽም ይነጋል ይነጋል ይህንን አውቃለሁ
እንደጨለመ አይቀር አይቀርም እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x)
እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉ (እግዚአብሔር)
እግዚአብሔር ቀን አለው (፬x)
|