ዝርግፍ ፡ ጌጤ (Zergef Gietie) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
አዝ፦ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ ነህ ፡ ኩራቴ
ኢየሱሴ ፡ ማዕረጌ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ (፬x)

እንደዐይኖችህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህልኝ
የከበደ ፡ ሸክሜን ፡ ከእኔ ፡ አራግፈህልኝ
ቀና ፡ ብዬ ፡ እንድኖር ፡ አንተ ፡ አድርገኸኛል
ከክብር ፡ ጋር ፡ ስፍራን ፡ ጌታ ፡ ሰጥተኸኛል
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
መመኪያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ማረፊያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ ነህ ፡ ኩራቴ
ኢየሱሴ ፡ ማዕረጌ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ (፬x)

እኔ ፡ ያላየሁትን ፡ አንተ ፡ አይተህልኝ
የሕይወቴን ፡ ጐዳና ፡ ያቀናናህልኝ
ከእኔ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ አንተ ፡ ታስባለህ
አላማህ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
መመኪያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ማረፊያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ ነህ ፡ ኩራቴ
ኢየሱሴ ፡ ማዕረጌ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ (፬x)

ያሰብከው ፡ ሆነልኝ ፡ አንተ ፡ ለእኔ ፡ ያልከው
አንተ ፡ ይሁን ፡ ስትል ፡ ጌታ ፡ ከልካይ ፡ ነው
ያሰብከው ፡ ይሆናል ፡ ያየኸው ፡ ይጸናል
እንደ ፡ ቃልህ ፡ ሆነህ ፡ ታምነህ ፡ ተገኝተሃል
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
መመኪያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ማረፊያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (፪x)