የጸና ፡ ግንብ (Yetsena Genb) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፭ (15)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
የጸና ፡ ግንብ ፡ የሕይወቴ ፡ ምርኩዝ ፡ ሞገሴ ፡ ነው ፡ ለእኔ
በእርሱ ፡ ብርታት ፡ በእርሱ ፡ ፀጋ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ጸንቼ ፡ መቆሜ
ተዐምረኛ ፡ የተዐምራት ፡ አምላክ ፡ ድንቅን ፡ የሚሰራ
ከጌታዬ ፡ ከኢየሱሴ ፡ በቀር ፡ የለም ፡ እውነተኛ

ታሪክ ፡ ተገልብጦ ፡ ጠላቴም ፡ ተመቶ
በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እርሱ ፡ ራሱ ፡ ገብቶ
ስላየሁ ፡ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል
ስላየሁ ፡ የኢየሱሴን ፡ ማዳን ፡ ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል
ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል
ለእርሱማ ፡ ምሥጋና ፡ ያንስበታል
(፪x)

የተጣለ ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳይጠፋ ፡ በምክሩ ፡ እያሰበ
ማክበር ፡ ያውቃል ፡ በፀጋ ፡ ላይ ፡ ፀጋ ፡ እይደራረበ
አይቻለሁ ፡ ይሄ ፡ በእኔ ፡ ሆኖ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ከአጠገቤ ፡ ቆሞ ፡ አለሁ ፡ ሲል ፡ ከጐኔ

ታሪክ ፡ ተገልብጦ ፡ ጠላቴም ፡ ተመቶ
በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እርሱ ፡ ራሱ ፡ ገብቶ
ስላየሁ ፡ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል
ስላየሁ ፡ የኢየሱሴን ፡ ማዳን ፡ ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል
ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል
ለእርሱማ ፡ ምሥጋና ፡ ያንስበታል
(፪x)

የበላይ ፡ ቢሉህ ፡ ቢያሞጋግሱህ
አንተን ፡ አይገልጹም ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ቢሉህ
የበላይ ፡ ብልህ ፡ ባሞጋግስህ
አንተን ፡ አልገልጽህ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ብልህ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህና (፬x)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ገናና
(፪x)

አይጓደል ፡ አምልኮዬ ፡ ለአንተ ፡ ለጌታዬ (፪x)
አይጓደል ፡ ምሥጋናዬ ፡ ለአንተ ፡ ለጌታዬ (፪x)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህና (፬x)
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትልቅ ፡ ነህ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ገናና
(፪x)