ይሄ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (Yehie New Yenie Gieta) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ ታሪኬን ፡ የለወጠው
መራራውን ፡ ያጣፈጠልኝ ፤ ሕይወቴን ፡ መልክ ፡ የሰጠው (፪x)
እኔስ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እኖርለታለሁ
ከኖርኩለት ፡ በላይ ፡ እኖርለታለሁ
እኔስ ፡ ለኢየሱሴ ፡ እኖርለታለሁ
ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ እሆንለታለሁ

ከልካዩ ፡ ከልክሎት ፡ ገድቦት ፡ ነው ፡ እንጂ
ሲያስገመግም ፡ መጥቶ ፡ ማዐበሉ ፡ ከደጅ
ነገር ፡ ተገልብጦ ፡ መርገሙ ፡ በባርኮት
ለሞት ፡ የታጨው ፡ ሰው ፡ በዝቶለታል ፡ ሕይወት

አዎ ፡ ልዘምርለት ፤ አዎ ፡ ልቀኝለት
አዎ ፡ በእርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ
እኔ ፡ ሰው ፡ የሆንኩት
ገና ፡ ስለእርሱ ፡ ክብር ፤ ገና ፡ ስለእርሱ ፡ ዝና
ገና ፡ እኔ ፡ ዘምሬ ፤ ገና ፡ መች ፡ ጠገብኩና
ገና ፡ ከሆንኩት ፡ በላይ ፤ ገና ፡ ብሆን ፡ ሲያንስ ፡ ነው
ገና ፡ ያደረገልኝን ፤ ገና ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው

በእሳት ፡ ውስጥ ፡ አለፌያለሁ ፡ አላቃጠለኝም
በውኃም ፡ አልፌያለሁ ፡ አላሰጠመኝም
ምህረቱ ፡ እንደጋሻ ፡ እየከለለኝ
የትላንትና ፡ ሃዘኔ ፡ ጌታ ፡ አስረሳኝ

ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር
ተመስገን ፡ ከማለት ፡ በቀር
እርሱ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ ያደረገኝ
ትላንትን ፡ እያሻገረኝ

ቀን ፡ አለህ ፡ ስለው ፡ ቀን ፡ ሰጠኝ
ከቀን ፡ በላይ ፡ ቀን ፡ አሳየኝ
ቀን ፡ በቀን ፡ ምህረቱ ፡ በዝቶ
አቆመኝ ፡ ቅኔውን ፡ ሞልቶ

አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ ታሪኬን ፡ የለወጠው
መራራውን ፡ ያጣፈጠልኝ ፤ ሕይወቴን ፡ መልክ ፡ የሰጠው (፪x)
እኔስ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እኖርለታለሁ
ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ እሆንለታለሁ
እኔስ ፡ ለኢየሱሴ ፡ እኖርለታለሁ
ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ እሆንለታለሁ

ደመናም ፡ ሳይታይ ፡ ንፋስም ፡ ሳይኖር
ሁሉን ፡ ከላይ ፡ አዞ ፡ የሚያሰማምር
ጌታ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ሁሌም ፡ ሁሉን ፡ ቻይ
በስራው ፡ ትክክል ፡ የሌለው ፡ ከልካይ

አዎ ፡ ልዘምርለት ፤ አዎ ፡ ልቀኝለት
አዎ ፡ በእርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ
እኔ ፡ ሰው ፡ የሆንኩት
ገና ፡ ስለእርሱ ፡ ክብር ፤ ገና ፡ ስለእርሱ ፡ ዝና
ገና ፡ እኔ ፡ ዘምሬ ፤ ገና ፡ መች ፡ ጠገብኩና
ገና ፡ ከሆንኩት ፡ በላይ ፤ ገና ፡ ብሆን ፡ ሲያንስ ፡ ነው
ገና ፡ ያደረገልኝን ፤ ገና ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው

ትሞትብኛለህ ፡ አልልም ፡ ሕያው ፡ ነህ
ትቀርብኛለህ ፡ አልልም ፡ ቅርቤ ፡ ነህ
ትከዳኛለህ ፡ ነህ ፡ አልልም ፡ ታማኝ ፡ ነህ
አምላኬ ፡ ከምንም ፡ ከማንም ፡ ልዩ ፡ ነህ

ልዩ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ልዩ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ልዩ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ (አንተ ፡ ልዩ)
ልዩ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ