ተወራርጃለሁ (Tewerarejalehu) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
አዝ፦ ተወራርጃለሁ ፡ እኔማ ፡ ያወጣኛል ፡ ብዬ
ተወራርጃለሁ ፡ እኔማ ፡ እርሱ ፡ አለልኝ ፡ ብዬ
ተወራርጃለሁ ፡ እኔማ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ ፡ ብዬ
ተወራርጃለሁ ፡ እኔማ ፡ አይጥለኝም ፡ ብዬ
አይጥልማ (አይጥልማ) ፡ አይረሳማ (አይረሳማ) (፪x)
ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ አይጥልማ
ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ አይረሳማ (፬x)

የይለፍ ፡ ቃል ፡ አለኝ ፡ ተሻገር ፡ ብሎኛል
ፋሬስ ፡ ብዬ ፡ ልውጣ ፡ ጌታ ፡ ቀድሞልኛል
የኋላዬን ፡ ሁሉ ፡ የኋሊት ፡ ረስቼ
ልገስግስ ፡ በእምነት ፡ ጌታን ፡ ተመኝቼ
ልሻገር ፡ በእምነት ፡ እርሱን ፡ ተመክቼ

ይታመናል ፡ ጌታ ፡ ይታመናል
ይይታመናል ፡ ኢየሱስ ፡ ይታመናል
ይታመናል ፡ ጌታ ፡ ይታመናል
ይታመናል ፡ እርሱ ፡ ይታመናል
(፫x)

ገና ፡ ለአንተ ፡ ክብር (ለአንተ ፡ ክብር)
ገና ፡ ለአንተ ፡ ዝና (ለአንተ ፡ ዝና)
ገና ፡ እዘምራለሁ (እዘምራለሁ)
ገና ፡ እንደገና (፪x)

ለእግዚአብሔር ፡ እኔማ ፡ ለእግዚአብሔር
አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ብዙ ፡ ክብር
ለኢየሱሴ ፡ እኔማ ፡ ለኢየሱሴ
አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ብዙ ፡ ውዳሴ
አለኝ ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ለአዳነኝ

ከእጆቹ ፡ ተዘግተው ፡ ሳለ ፡ ኢየሱስ ፡ መጣ
ጠላቴ ፡ መሸበት ፡ ለእኔ ፡ ሌቱ ፡ ነጋ
የተናገረኝን ፡ እስከሚፈጽመው
አይጥለኝም ፡ አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው
አይተወኝም ፡ አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው

ይታመናል ፡ ጌታ ፡ ይታመናል
ይይታመናል ፡ ኢየሱስ ፡ ይታመናል
ይታመናል ፡ ጌታ ፡ ይታመናል
ይታመናል ፡ እርሱ ፡ ይታመናል
(፫x)

አዝ፦ ተወራርጃለሁ ፡ እኔማ ፡ ያወጣኛል ፡ ብዬ
ተወራርጃለሁ ፡ እኔማ ፡ እርሱ ፡ አለልኝ ፡ ብዬ
ተወራርጃለሁ ፡ እኔማ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ ፡ ብዬ
ተወራርጃለሁ ፡ እኔማ ፡ አይጥለኝም ፡ ብዬ
አይጥልማ (አይጥልማ) ፡ አይረሳማ (አይረሳማ) (፪x)
ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ አይጥልማ
ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ አይረሳማ (፪x)