ሰው ፡ አይጥልም (Sew Aytelem) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ (2011)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
በድንገት ፡ ደረስክልኝ ፡ ሃዘኔን ፡ ገፈፍክልኝ
ጨለማው ፡ አላቆመኝ ፡ በባርኮት ፡ ቤቴ ፡ ገባህ
በሰላም ፡ ቤቴ ፡ ገባህ (፪x)
በክብርህ ፡ ቤቴ ፡ ገባህ (፪x)

እርሱን ፡ ታምኜ ፡ የምን ፡ ሥጋት
ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ አባት
ጌታዬን ፡ ይዤ ፡ የምን ፡ ሥጋት
ቁልፉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ አባት
ጌታ ፡ እያለ ፡ የምን ፡ ሥጋት
ቁልፉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ አባት
ጌታዬን ፡ ይዤ ፡ የምን ፡ ሥጋት
ቁልፉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ አባት

አዝ፦ ሰው ፡ አይጥልም ፡ ጌታ ፡ ያነሳል ፡ እጅ ፡ ይዞ
የጠላትን ፡ ወጥመድ ፡ እቅድ ፡ አፈራርሶ
እኔን ፡ አልጣለኝም ፡ ማንን ፡ እንደጣለ
በእጁ ፡ መዳፍ ፡ ይዞኝ ፡ አለሁኝ ፡ ስላለኝ

ይሄው ፡ ሳይለወጥ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አለ
ይሄው ፡ ሳይቀየት ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አለ
ጌታ ፡ አይለወጥም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አለ
እርሱ ፡ አይለወጥም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አለ

ጌታ ፡ አይለወጥም ፡ በዙፋኑ ፡ አለ (፪x)
ጌታ ፡ አይቀየርም ፡ በዙፋኑ ፡ አለ
እርሱ ፡ አይቀየርም ፡ በዙፋኑ ፡ አለ

አንገቴን ፡ አልደፋም ፡ በቃ ፡ በቃ ፡ አምላክ ፡ አለኝ
ስጠራው ፡ በጥኖ ፡ ደርሶ ፡ አለሁ ፡ የሚለኝ
ሰው ፡ አይሆንም ፡ ሲሉኝ ፡ ጌት ፡ አሰው ፡ አድርጐኛል
ሰው ፡ የማይጥል ፡ እኮ ፡ ይዞኝ ፡ ወስዶ ፡ አኑሮኛል

አለልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ አለልኝ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ
አልልን ፡ የእኔ ፡ ንጉሥ ፤ አለልኝ ፡ ደጉ ፡ ኢየሱስ
አለልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ አለልኝ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ
አልልን ፡ የእኔ ፡ ንጉሥ ፤ ሰው ፡ ማይጥል ፡ ደጉ ፡ ኢየሱስ

ዱካ ፡ ሳይታይ ፡ ፍለጋ ፡ ደርሰህልኛል
ማንም ፡ የለም ፡ ስልህ ፡ ከጐኔ ፡ አንተ ፡ ቆመሃል
በዚያ ፡ ቀውጢ ፡ ቀን ፡ ስጠራህ ፡ የታለህ ፡ ብዬ
ሰው ፡ የማይጥለውን ፡ እጅህን ፡ አየሁ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ሰው ፡ አይጥልም ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ አይጥልም (፪x)
ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፪x)

የዘገየ ፡ ሲመስል ፡ ጉብኝትህ??? ፡ ሲረዝም
ለማየት ፡ ሲቸግር ፡ የሚጠብቁት ፡ ህልም
የሌሊትይ ፡ ድካም ፡ ጫናው ፡ ሲበረታ
በተዘጋው ፡ ደጅ ፡ ውስጥ ፡ መውጫ ፡ ያሳያል ፡ ጌታ
በተዘጋው ፡ ደጅ ፡ ውስጥ ፡ መውጫ ፡ ያሳያል ፡ ጌታ (፪x)
በተዘጋው ፡ ደጅ ፡ ውስጥ ፡ መውጫ ፡ አለው ፡ ጌታ (፪x)

በራሱ ፡ ተራ ፡ ይሆናል ፡ ይህን ፡ አምናለሁ
ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆኖ ፡ ተስፋዬን ፡ በአካል ፡ እወርሰዋለሁ
ያለው ፡ ለማይቀር ፡ እግዚአብሔር ፡ በእኔ ፡ የተናገረው
ልሻገር ፡ በእምነት ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ አይለወጥም

አዝ፦ ሰው ፡ አይጥልም ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ አይጥልም (፪x)
ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፪x)