መታመኛዬ (Metamegnayie) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
መታመኛዬ ፡ መታመኛዬ

እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ አለ
ሁሉንም ፡ አዲስ ፡ የሚያደርገው
ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ ድንገት ፡ ከተፍ ፡ የሚል
ታሪክን ፡ በታሪክ ፡ ሚሽረው
ጌታ ፡ ነው ፡ የሁሉ ፡ ቁልፍ ፡ ያለው
ጌታ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ ምታመነው
ጌታ ፡ ነው ፡ ድንገት ፡ ከተፍ ፡ የሚል
ጌታ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሚቻለው

ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ ፡ በአንተ ፡ ተማምኜ (፪x)
እጅግ ፡ በሚመቸው ፡ ትከሻ ፡ ላይ ፡ ሆኜ (፪x)
ተራሮች ፡ ቢወርዱ ፡ ወደባሕር ፡ ልብ (፪x)
የያዝኩት ፡ አንተን ፡ ነው ፡ የነፍሴ ፡ መልህቅ (፪x)

የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የሕይወት ፡ መገኛ
ጽኑ ፡ ግንብ ፡ ሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ መታመኛ (፪x)
መታመኛ ፡ መመኪያዬ ፡ እኔ ፡ አለኝ ፡ የምለው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ
የእኔ ፡ ጋሻ ፡ ማምለጫዬ ፡ የዘለዓለም ፡ ክብሬ ፡ ሆነኝ ፡ አለኝታዬ
መመኪያዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፬x)

የድል ፡ መሰረቴ ፡ መደላደላዬ (፪x)
እንድኖር ፡ ያደረከኝ ፡ በአንተ ፡ እፎይ ፡ ብዬ (፪x)
ጀርባ ፡ አልሰጠኸኝም ፡ በጠላቴ ፡ ፊት ፤ በሚጠላኝ ፡ ጊት
ይልቁን ፡ ቀባኸኝ ፡ ራሴን ፡ በዘይት (፪x)

ነፍሴን ፡ በከበረው ፡ ሰረገላ ፡ አስቀምጠህ ፡ ሞላኸኝ ፡ በምሥጋና
የእኔ ፡ ጌታ ፡ እንደአንተማ ፡ ለእኔ ፡ ማንም ፡ የለም
ሾሜሃለሁ ፡ ግዛ ፡ በሕይወቴ ፡ ለዘለዓለም
ኢየሱሴ ፡ እንደ ፡ አንተማ ፡ ለእኒ ፡ ማንም ፡ የለም
ሾሜሃለሁ ፡ ግዛ ፡ በሕይወቴ ፡ ለዘለዓለም
መታመኛ ፡ መታመኛዬ ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ (፬x)

የታል ፡ የትናንቱ ፡ የከበደኝ ፡ ነገር (፪x)
እንደጉም ፡ በነነ ፡ ከላይ ፡ ስትናገር (፪x)
አዲስ ፡ የድል ፡ ምዕራፍ ፡ ተቀዳጅቻለሁ (፪x)
በአንተ ፡ በአምላኬ ፡ ቅጥሩን ፡ ዘልያለሁ (፪x)

የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የሕይወት ፡ መገኛ
ጽኑ ፡ ግንብ ፡ ሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ መታመኛ (፪x)
መታመኛ ፡ መታመኛዬ ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ (፬x)