From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
መንፈስህን ፡ ከእኔ ፡ አትውሰድብኝ (፬x)
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝ
እንደ ፡ አንተ ፡ ሚሆንልኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሚሆንልኝ
የውስጡ ፡ ቆሽሾ ፡ ውጪውን ፡ አጥርቼ
ትንኝ ፡ ያጠራው ፡ ግመል ፡ ያክል ፡ ውጬ
ለሰው ፡ ታይታ ፡ ሚኖር ፡ ፈሪሳዊ ፡ ሆኜ
ማለፍን ፡ አልሻም ፡ ከክብርህ ፡ ጐድዬ
አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
በፊትህ ፡ ራሴን ፡ ላሳይ
አግዘኝ ፡ እጠራሃለሁ
ቸር ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ አውቅሃለው (፪x)
አትተወኝ ፡ አትጣለኝ
ያላንተማ ፡ ሕይወት ፡ የለኝ (፬x)
እንደልቤ ፡ ሳይሆን ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ
ልወረስ ፡ በክብርህ ፡ እጄን ፡ ይያዝ ፡ እጅህ
መንፈስህ ፡ መሪዬ ፡ ይሁን ፡ እረኛዬ
በእቅፍህ ፡ ውስጥ ፡ ነው ፡ ክብሬም ፡ ዋስትናዬ
አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
በፊትህ ፡ ራሴን ፡ ላሳይ
አግዘኝ ፡ እጠራሃለሁ
ቸር ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ አውቅሃለው (፪x)
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ነህ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የልቤ ፡ ማረፊያ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሌላ ፡ አልመኝም
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አጽናኝ ፡ ከአንተ ፡ ወዲያ
አትተወኝ ፡ አትጣለኝ
ያላንተማ ፡ ሕይወት ፡ የለኝ (፬x)
|