ምድረበዳው (Medrebedaw) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
አዝ፦ ምድረበዳው ፡ ተዐምር ፡ መሥሪያ ፡ ነው ፣
ባዶ ፡ ነገር ፡ ሙላትን ፡ ያያል ፤
ሰው ፡ አለቀ ፡ አበቃ ፡ ሲል ፣
የአንተ ፡ ተዐምር ፡ ይጀምራል ።
አየሁ ፡ በዐይኔ ፡ የአንተን ፡ በጐነት ፣
በቀን ፡ በሌት ፡ ክንድህ ፡ ሲረዳኝ ፤
በማዕበሉ ፡ በወጀቡ ፡ ላይ ፣
ከፊት ፡ ቀድመህ ፡ በድል ፡ ስትመራኝ ። (፪x)

አይቼሃለሁ ፡ ከወዳጅ ፡ ይልቅ ፡ ወዳጅ ፡ የሆንከኝ
አይቼሃለሁ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ክብር ፡ ያሳየኸኝ
አይቼሃለሁ ፡ ይሆናል ፡ ያልክልኝ ፡ ሆኗል ፡ በሕይወቴ
አይቼሃለሁ ፡ ድካሜን ፡ ሽረህ ፡ ሆንከኝ ፡ ጉልበቴ

ያሰበውን ፡ ያቀደውን ፡ በሕይወቴ ፡ ፈጸመና
ድንቅን ፡ ሰርቶ ፡ አስደነቀኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እንደገና
አዲስ ፡ ታሪክ ፡ አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ ጽፎ ፡ ሰጠኝ ፡ ከሰማይ
እርሱ ፡ ካለ ፡ ሆነ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የለበት ፡ አዝዥ ፡ ከልካይ

በአንተ ፡ መታመኔ ፡ አዋጣኝ ፡ ጌታዬ
አላፈርኩብህም ፡ ያዋጣኛል ፡ ብዬ
ጠላቴም ፡ ወዳጄ ፡ ግርም ፡ እስከሚለው
ይሄው ፡ ተዐምርህን ፡ በዘመኔ ፡ አየሁ (፪x)

አዝ፦ ምድረበዳው ፡ ተዐምር ፡ መሥሪያ ፡ ነው ፣
ባዶ ፡ ነገር ፡ ሙላትን ፡ ያያል ፤
ሰው ፡ አለቀ ፡ አበቃ ፡ ሲል ፣
የአንተ ፡ ተዐምር ፡ ይጀምራል ።
አየሁ ፡ በዐይኔ ፡ የአንተን ፡ በጐነት ፣
በቀን ፡ በሌት ፡ ክንድህ ፡ ሲረዳኝ ፤
በማዕበሉ ፡ በወጀቡ ፡ ላይ ፣
ከፊት ፡ ቀድመህ ፡ በድል ፡ ስትመራኝ ። (፪x)

አይቼሃለሁ ፡ ከወዳጅ ፡ ይልቅ ፡ ወዳጅ ፡ የሆንከኝ
አይቼሃለሁ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ክብር ፡ ያሳየኸኝ
አይቼሃለሁ ፡ ይሆናል ፡ ያልክልኝ ፡ ሆኗል ፡ በሕይወቴ
አይቼሃለሁ ፡ ድካሜን ፡ ሽረህ ፡ ሆንከኝ ፡ ጉልበቴ

በአንተ ፡ እጅ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ ነገር
የሁሉ ፡ ቁልፍ ፡ የአንተ ፡ ብቻ
ይሁን ፡ ያልከው ፡ ሲሆንልህ ፡ አይቻለሁ ፡ የለህ ፡ አቻ
ሞተውን ፡ ያበቃውን ፡ ቃል ፡ አውጥተህ ፡ ትጥራለህ
ተዘጋው ፡ ደጅ ፡ ገብተህ ፡ ሰላምህን ፡ ታውጃለህ

በአንተ ፡ መታመኔ ፡ አዋጣኝ ፡ ጌታዬ
አላፈርኩብህም ፡ ያዋጣኛል ፡ ብዬ
ጠላቴም ፡ ወዳጄ ፡ ግርም ፡ እስከሚለው
ይሄው ፡ ተዐምርህን ፡ በዘመኔ ፡ አየሁ (፪x)

አዝ፦ ምድረበዳው ፡ ተዐምር ፡ መሥሪያ ፡ ነው ፣
ባዶ ፡ ነገር ፡ ሙላትን ፡ ያያል ፤
ሰው ፡ አለቀ ፡ አበቃ ፡ ሲል ፣
የአንተ ፡ ተዐምር ፡ ይጀምራል ።
አየሁ ፡ በዐይኔ ፡ የአንተን ፡ በጐነት ፣
በቀን ፡ በሌት ፡ ክንድህ ፡ ሲረዳኝ ፤
በማዕበሉ ፡ በወጀቡ ፡ ላይ ፣
ከፊት ፡ ቀድመህ ፡ በድል ፡ ስትመራኝ ። (፪x)

አይቼሃለሁ ፡ ከወዳጅ ፡ ይልቅ ፡ ወዳጅ ፡ የሆንከኝ
አይቼሃለሁ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ክብር ፡ ያሳየኸኝ
አይቼሃለሁ ፡ ይሆናል ፡ ያልክልኝ ፡ ሆኗል ፡ በሕይወቴ
አይቼሃለሁ ፡ ድካሜን ፡ ሽረህ ፡ ሆንከኝ ፡ ጉልበቴ