ሌሊቱ ፡ ነጋ (Lielitu Nega) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
ብርሃን ፡ ሆነ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ
አዋጅ ፡ ተሰማኝ ፡ ከአሪያም ፡ የወጣ
ጌታ ፡ አላለፈኝ ፡ ገባ ፡ ከቤቴ
ልዘምርለት ፡ ሞልቷል ፡ ስለቴ

ስራዬን ፡ ሰርቶልኝ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ አልዘምር
ሁሉን ፡ ለአደረገው ፡ ይሁንለት ፡ ክብር
ጠላቴን ፡ ጥሎልኝ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ አልዘምር
ሁሉን ፡ ለአደረገው ፡ ይሁንለት ፡ ክብር
ይሁንለት ፡ ክብር (፰x)

እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ መልካም
በክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሸጊያ ፡ እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የለም (፪x)
እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የለም (፰x)

አይልኝ ፡ አይልኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ ፡ ፈረደልኝ
የጠላቴን ፡ ዛቻ ፡ ከንቱ ፡ አደረገልኝ (፪x)

ፎክሮስ ፡ ነበር ፡ ጠላት ፡ በእኔ ፡ ላይ
ጌታ ፡ ገልብጦት ፡ ቆምኩኝ ፡ እራሱ ፡ ላይ
ድል ፡ አስለመደኝ ፡ ድል ፡ አየሁ ፡ በዐይኔ
አከብረዋለሁ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ክብሬ
እርሱ ፡ ነው ፡ ክብሬ (፰x)

ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ የመገለጫ
ከአለት ፡ ንቃቃት ፡ በክብር ፡ መውጫ
የይልፈን ፡ ቃል ፡ ሰጠኝ ፡ ጌታዬ
ልውጣ ፡ ልገለጥ ፡ በምሥጋናዬ

ስራዬን/ጠላቴን ፡ ሰርቶልኝ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ አልዘምር
ሁሉን ፡ ላደረገው ፡ ይሁንለት ፡ ክብር (፪x)
ይሁንለት ፡ ክብር (ይሁንለት) (፰x)