From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እግዚአብሔር ፡ በድንቅ ፡ የረዳው (ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው) (፫x)
ሞቷል ፡ ሲባል ፡ ሕይወት ፡ ያየ ፡ ሰዉ (ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው) (፫x)
የጠላቱን ፡ ውድቀት ፡ ያየ ፡ ሰዉ (ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው) (፫x)
ጌታ ፡ ከላይ ፡ ተሻገር ፡ ያለዉ (ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው) (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ቢኮሩበት ፡ ያኮራል
ስሙ ፡ ከስም ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ሲጠሩት ፡ ያስመልጣል
ኮራ ፡ ብዪ ፡ እኖራለሁ ፡ ያመንኩትን ፡ አውቃለሁ
ሹመቴ ፡ ሽልማቴ ፡ ከፍታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አዝ፦ ከፍታዬ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ከፍታዬ (፬x)
ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ ተነሳ (እንደገና) (፫x)
በእርሱ ፡ ያለፍኩትን ፡ ያን ፡ ቀን ፡ አሰበና (እንደገና) (፪x)
አምልኮ ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ ተነሳ (እንደገና) (፫x)
እርሱ ፡ ያደረገልኝን ፡ ዉለታ ፡ አሰበና (እንደገና) (፪x)
ገና ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ገና
ለአንተ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
ዉለታህ ፡ አለብኝና (፪x)
ዉለታ ፡ አለብኝና (፰x)
ያየሁትን ፡ ሳላይ ፡ አልቀርም ፡ መንገድ ፡ ላይ
እደርሳለሁ ፡ ከግቤ ፡ ህልም ፡ አለኝ ፡ ከሰማይ
ሰው ፡ አይደለምና ፡ የተናገረኝ
የጠራኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ቃሉን ፡ የሰጠኝ
ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ ፡ ያውም ፡ በክብር
ራዕዩን ፡ የሰጠ ፡ አለና ፡ እግዚአብሔር
ሰረገላው ፡ ከደጅ ፡ ቆሟል ፡ ለማስረጃ
ይሄው ፡ ዘመን ፡ መጣ ፡ ወደክብር ፡ መውጫ
አዝ፦ ከፍታዬ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ከፍታዬ (፬x)
ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ በልጁ ፡ ወዶኛል
ልክደው ፡ የማልችለው ፡ ይህ ፡ እውነት ፡ ገብቶኛል
የብረቱ ፡ መዝጊያ ፡ ምን ፡ ቢቆም ፡ ከፊቴ
አውቆ ፡ ይከፈታል ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከፊቴ
ንጉሥ ፡ የወርቁን ፡ ዘንግ ፡ ዘረጋልኝና
ያለህግ ፡ አስገባኝ ፡ ከፋፈተውና
ገና ፡ ሳልናገር ፡ ሁሉ ፡ ተሰካካ
የታመንኩት ፡ አምላክ ፡ ቀድሞ ፡ ወጥቷል ፡ ለካ
አዝ፦ ከፍታዬ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ከፍታዬ (፬x)
|