ኢየሱስ (Eyesus) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
አይታለፍም ፡ ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ነበረ
ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ተውቦ ፡ ሰመረ
ምን ፡ ይሳንሃል ፡ ሁሉን ፡ ልጸራው ፡ ችለሃል
ተራራውንም ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ አርገሃል

(ኢየሱስ) ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ ፡ አንተ
(ኢየሱስ) ፡ ትርጉም ፡ ማንነቴ
(ኢየሱስ) ፡ በቀኝህ ፡ ያኖርከኝ
(ኢየሱስ) ፡ የልቤ ፡ ኩራቴ
(ኢየሱስ) ፡ ምሥጋናዬ ፡ አንተ ፡ ነህ
(ኢየሱስ) ፡ አንተን ፡ እጠራለሁ
(ኢየሱስ) ፡ ስምህ ፡ ሲያለመልም
(ኢየሱስ) ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው

አምላክ ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ የማያልፍ ፡ የለም
ምርኩዜ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሸንበቆ ፡ አይደለህ
ትላንት ፡ ያደረከው ፡ እምነት ፡ ሆኖኛል
የማይጥል ፡ እጅህ ፡ እጄን ፡ ይዞኛል
አልተረታሁም ፡ እኔስ ፡ በስምህ ፡ ተወረርጄ
ፊቴ ፡ አላፈረም ፡ መልሴ ፡ ፈጠነ ፡ ገባልኝ ፡ ከእጄ
የማይቻለው ፡ በአንተ ፡ ተችሎ ፡ አይቼዋለሁ
ለስምህ ፡ ክብር ፡ ለጌትነትህ ፡ እዘምራለሁ

አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የምለው ፤ አለኝ ፡ ውስጤ ፡ ሚወደው
አለኝ ፡ ሚስጥረኛዬ ፤ ሳይንቅ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ
አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የምለው ፤ አለኝ ፡ ውስጤ ፡ ሚወደው
አለኝ ፡ ሚስጥረኛዬ ፤ ኢየሱስ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ
ኢየሱስ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ (፬x)

እረኛዬ ፡ ነህ ፡ ከአንበሳው ፡ ከድብ ፡ አድነኸኛል
አበቃ ፡ ሲባል ፡ የሁሉንም ፡ ቁልፍ ፡ ይዘህ ፡ ደርሰሃል
ታዲያ ፡ ብዘምር ፡ ከሆንኩት ፡ በላይ ፡ መች ፡ ይበዛና
ታሪኬ ፡ ሆነህ ፡ አዳፋ ፡ ልብሴን ፡ ጥለሃልና

አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የምለው ፤ አለኝ ፡ ውስጤ ፡ ሚወደው
አለኝ ፡ ሚስጥረኛዬ ፤ ሳይንቅ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ
አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የምለው ፤ አለኝ ፡ ውስጤ ፡ ሚወደው
አለኝ ፡ ሚስጥረኛዬ ፤ ኢየሱስ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ
ኢየሱስ ፡ ገብቷል ፡ ጓዳዬ (፬x)