እሱ ፡ ትልቅ ፡ ሆኖ (Esu Teleq Hono) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
እሱ ፡ ትልቅ ፡ ሆኖ ፡ ትንሽ ፡ አላስብም
ማመስገኔን ፡ ትቼ ፡ አላጉረመርምም
ይሆናል ፡ እንዳለኝ ፡ ይሆናል ፡ እላለሁ
ተስፋውን ፡ እየሰጠሁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው
ታማኝ ፡ ነዉ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው (፬x)

እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሆናል
እንዳሰበው ፡ ሁሉ ፡ ይፈጸማል
ያደርገዋል ፡ ብዬ ፡ ተደግፌዋለሁ
እንደተናገረኝ ፡ ይሆናል ፡ አምናለሁ
ይሰራዋል ፡ ብዬ ፡ ተደርፌዋለሁ
እንደተናገረኝ ፡ ይሆናል ፡ አምናለሁ

በእርሱ ፡ ስራ ፡ ጣልቃ ፡ አልገባም ፡ እግዚአብሔር ፡ ልክ ፡ ነው
እስማማለሁ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው
ባይገባኝም ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ለእኔ ፡ ቢሆን ፡ ግራ
እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ያውቃል ፡ ልቁም ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ

ትክክል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ትክክል ፡ ነው (ትክክል ፡ ነው)
ትክክል ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ትክክል ፡ ነው (ትክክል ፡ ነው)
አዋቂ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (አዋቂ ፡ ነው)
አዋቂ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ አዋቂ ፡ ነው (አዋቂ ፡ ነው)

ሁሉን ፡ ደርሶ ፡ ውብ ፡ ሊያደርገው ፡ ጌት ፡ በጊዜው
ማጉረምረሜ ፡ ለምንድንነው ፡ እስኪ ፡ ላምልከው
ትላንትና ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ማኅተሙም ፡ ያኔ ፡ ፈታህ ፡ ዛሬም ፡ እልሻዳይ ፡ ነው

ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው (ኤሻዳይ ፡ ነው) (፪x)
ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነው (ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነው) (፪x)
ኤልሻዳዬ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)
አዶናዬ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)