አቀላልቷል ፡ ሰማዩ (Aqelaltual Semayu) - ካሳሁን ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሳሁን ፡ ለማ
(Kassahun Lemma)

Kasahun Lema 3.jpg


(3)

አቀላልቷል ፡ ሰማዩ
(Aqelaltual Semayu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሳሁን ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Kassahun Lemma)

 
አዝ፦ አቀላልቷል ፡ ሰማዩ ፡ ሊሰናበት ፡ ሌቱ
ምን ፡ ጭጋጉ ፡ ቢያይል ፡ አይቀርም ፡ መንጋቱ
ብርሃን ፡ ዘንበል ፡ ቢል ፡ ቢዳምን ፡ ደመና
አዲስ ፡ ቀን ፡ ያሳያል ፡ ጌታ ፡ ቸር ፡ ነውና (፪x)

አሃሃ ፡ አንተን ፡ ታምኖ ፡ ማንስ ፡ ወድቆ ፡ ቀርቷል
አሃሃ ፡ የታመነህ ፡ ሁሉን ፡ ጥሶ ፡ አልፏል
አሃሃ ፡ መመኪያ ፡ ነህ ፡ ለምስኪኑ ፡ ጋሻ
አሃሃ ፡ ማምለጫ ፡ ነህ ፡ ከጥፋት ፡ መሸሻ

የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
የእኔ ፡ ንጉሥ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ
በድካሜ ፡ ያልሳቅክብኝ ፡ እምባዬንም ፡ ያበስክልኝ
ሳጸለቸኝ ፡ ተሸከምከኝ ፡ ከእናት ፡ ከአባት ፡ በላይ ፡ ሆንከኝ
ኢየሱስ (፫x) ፡ ከፍ ፡ በልልኝ (፪x)

አባት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ ከአባትም ፡ አባት
ያዋጣኛል ፡ ብዬ ፡ ያላፈርኩበት ፤ ያላፈርኩበት (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ከአየልኝ ፡ ከቶ ፡ አንድም ፡ አይጐድልም
አምላኬ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ሁኔታን ፡ አላይም
እጠብቀዋለሁ ፡ በስፍራዬ ፡ ሆኜ
ያለውን ፡ ያደርጋል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሆናል
እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይጸናል
እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሳካል
(፪x)

አዝ፦ አቀላልቷል ፡ ሰማዩ ፡ ሊሰናበት ፡ ሌቱ
ምን ፡ ጭጋጉ ፡ ቢያይል ፡ አይቀርም ፡ መንጋቱ
ብርሃን ፡ ዘንበል ፡ ቢል ፡ ቢዳምን ፡ ደመና
አዲስ ፡ ቀን ፡ ያሳያል ፡ ጌታ ፡ ቸር ፡ ነውና (፪x)