From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ምነው ፡ ሰማያትን ፡ ቀደህ ፡ ብትወርድልኝ
ብዬ ፡ እኔ ፡ ስጣራ ፡ ታየኛለህ (፪x)
ለካስ ፡ ታየኛለህ ፡ ከሰማያት ፡ በላይ
ለእኔ ፡ የምትራራ ፡ ታየኛለህ (፪x)
ያልተጠባበኩት ፡ የክብርህን ፡ ስራ
ገልጸህ ፡ ልታሳየኝ ፡ ታየኛለህ (፪x)
አሁን ፡ ተረዳሁት ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው
የአንተ ፡ አላማ ፡ ገባኝ ፡ ታየኛለህ (፪x)
ታየኛለህ ፡ ስጠራህ ፡ ትሰማኛለህ
ታየኛለህ ፡ የልቤን ፡ ታደምጠኛለህ
ታየኛለህ ፡ የደምህ ፡ ኪዳን ፡ አለኝ
ታየኛለህ ፡ ላትጥለኝ ፡ ስለያዝከኝ
ኢየሱስ (፪x) (ኢየሱሴ) ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋሴ (ለእኔ ፡ ዋሴ)
ፍቅርህን ፡ አስባለሁ (ፍቅርህን ፡ አስባለሁ) ፡ ዘለዓለም ፡ እወድሃለሁ (ዘለዓለም ፡ ወድሃለሁ) (፪x)
አምንሃለሁ ፡ አትጥልም ፡ አንተ ፡ አትጐዳም
አምንሃለሁ ፡ ጀርባ ፡ አትሰጥም ፡ ደርሰህ ፡ እንደባዳ
አምንሃለሁ ፡ መጠጋት ፡ ማቀፍ ፡ ባሕሪህ
አምንሃለሁ ፡ ተመካሁ ፡ በማይጥል ፡ ፍቅርህ (፪x)
ኢየሱስ (፪x) (ኢየሱሴ) ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋሴ (ለእኔ ፡ ዋሴ)
ፍቅርህን ፡ አስባለሁ (ፍቅርህን ፡ አስባለሁ) ፡ ዘለዓለም ፡ እወድሃለሁ (ዘለዓለም ፡ ወድሃለሁ) (፪x)
አምንሃለሁ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ከምንም ፡ በላይ
አምንሃለሁ ፡ ቃል ፡ ሳይሆን ፡ የልብን ፡ የምታይ
አምንሃለሁ ፡ እንደሰው ፡ አይተህ ፡ አተፈርድም
አምንሃለሁ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ጥለህ ፡ አትሄድም (፪x)
ምነው ፡ ሰማያትን ፡ ቀደህ ፡ ብትወርድልኝ ፡
ብዬ ፡ እኔ ፡ ስጣራ ፡ ታየኛለህ (፪x)
ለካስ ፡ ታየኛለህ ፡ ከሰማያት ፡ በላይ
ለእኔ ፡ የምትራራ ፡ ታየኛለህ (፪x)
ያልተጠባበኩት ፡ የክብርህን ፡ ስራ
ገልጸህ ፡ ልታሳየኝ ፡ ታየኛለህ (፪x)
አሁን ፡ ተረዳሁት ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው
የአንተ ፡ አላማ ፡ ገባኝ ፡ ታየኛለህ (፪x)
ታየኛለህ ፡ ስጠራህ ፡ ትሰማኛለህ
ታየኛለህ ፡ የልቤን ፡ ታደምጠኛለህ
ታየኛለህ ፡ የደምህ ፡ ኪዳን ፡ አለኝ
ታየኛለህ ፡ ላትጥለኝ ፡ ስለያዝከኝ
|