From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የእውነት ፡ መልክ ፡ ያለው ፡ ከእውነት ፡ የተጣላ
የጊዜውን ፡ ያየ ፡ የነገው ፡ ተላላ
በሌላው ፡ ላይ ፡ ፈራጅ ፡ ጣቶቹን ፡ ቀሳሪ
ስለእራሱ ፡ ኑሮ ፡ ሕያውን ፡ ቀባሪ
ካባው ፡ የሸፈነው ፡ መቃብርነቱን
የምላሱ ፡ ቂቤ ፡ አጥምዶ ፡ አረካለት
የልብ ፡ አውሬነቱን
አዝ፦ አድኅነነ ፡ ከመዐቱ ፡ ሰውረነ ፣
ስማነ ፡ አምላክነ ፡ ወመድኃኒነ (፪x)
(ይቅርብኝ) ፡ ላይጠቅመኝ ፡ ይቅርብኝ
(ይቅርብኝ) ፡ ቢቀርብኝ ፡ ሞት ፡ ነው
(ይቅርብኝ) ፡ ለካ ፡ የተወዳጀኝ
(ይቅርብኝ) ፡ ተንቀሳቃሽ ፡ ሞት ፡ ነው
(ይቅርብኝ) ፡ የፍቅር ፡ ሰው ፡ መሳይ
(ይቅርብኝ) ፡ የወንድም ፡ አታላይ
(ይቅርብኝ) ፡ ስንቱን ፡ ወጥቶ ፡ ጣለው
(ይቅርብኝ) ፡ ያልብሾት ፡ ተናኝ
ታረቅ ፡ ከራስህ ፡ ጋር ፡ ወገኔ
ሁሉ ፡ ያመልጥሃል ፡ ስትል ፡ ለእኔ ፣
መኖር ፡ ልመድ ፡ እንጂ ፡ ለሌላዉ
ያ ፡ ነው ፡ የሕይወት ፡ ተድላ ፡ ደስታዉ ።(፪x)
አዝ፦ አድኅነነ ፡ ከመዐቱ ፡ ሰውረነ ፣
ስማነ ፡ አምላክነ ፡ ወመድኃኒነ (፪x)
ጣኦት ፡ ተሰይፎ ፡ መቅደሽን ፡ ይዘርፋል
ሕሊናህን ፡ ጥሶት ፡ አካልህ ፡ ይሮጣል
ልጓም ፡ አበጂለት ፡ ራስህ ፡ ከአንተ ፡ ወጥቷል
ሁለት ፡ ሰው ፡ ሆነህ ፡ መታወቂያህ ፡ ጠፍቷል
ሩቅ ፡ አሳቢ ፡ ሆነህ ፡ በቅርቡ ፡ አዳሪ
የአፍ ፡ ብቻ ፡ አርበኛ ፡ አስጐምጅቶ ፡ በላ
አንቱ ፡ ፈሪሳዊ
እኔነቴን ፥ በእኔው ፡ ያለ ፡ የእኔው ፡ ጠላቴ ፣
አላወጣው ፡ ውስጤ ፡ በእኔው ፡ ነዋሪ ፡ ቤቴ
ኖሮ ፡ እንዳያጠፋኝ ፡ ንቃልኝ ፡ ውስጠቴን (፪x)
ማረን ፡ ማረን ፡ ይቅር ፡ በለን
ስማን ፡ ስማን ፡ ተቀበለን (፪x)
|