From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
ቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን (Kalkidan Tilahun)
|
|
፫ (3)
|
ይታየኛል ፡ ብዙ ፡ ነገር (Yetayegnal Bezu Neger)
|
ቁጥር (Track):
|
፰ (8)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች (Albums by Kalkidan Tilahun)
|
|
አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x)
እንደ ፡ ጥል ፡ ሆንክልኝ ፡ እንደ ፡ አበባ ፡ አበብኩኝ
እንደ ፡ ሊባኖስ ፡ ስሬ ፡ በቤትህ ፡ ሥር ፡ ሰደድኩኝ
እንደ ፡ ወይራ ፡ ውበት ፡ እንደ ፡ መዓዛዉ
በእኔ ፡ ያስቀመጥከው ፡ ዓለምን ፡ ሞላዉ (፪x)
አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x)
እንደ ፡ ዘንባባ ፡ ዛፍ ፡ እያሳደገኝ
ፍሬዬን፡ አበዛው ፡ አለመለመኝ
እንደ ፡ ረካች ፡ ገነት ፡ አምላኬ ፡ አደረገኝ
በብዛት ፡ በብዛት ፡ በብዛት ፡ ባርኮኝ
አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x)
እንደ ፡ ጠዋት ፡ ፀሐይ ፡ እንደሚያበራዉ
የጻድቃንም ፡ መንገድ ፡ እንደዚሁ ፡ ነዉ
ሙሉ ፡ ቀን ፡ እስኪሆን ፡ ገና ፡ ይጨምራል
የእኔም ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፡ እነሆ ፡ እንዲህ ፡ ሆኗል
አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x)
በውኑ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ የሚሳነው ፡ አለ ፡ ወይ
የሥጋ ፡ ለባሽ ፡ አምላክ ፡ የሚያቅተው ፡ አለ ፡ ወይ (፪x)
ልቤ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ጸና (፬x)
እርሱን ፡ ተማመነ ፡ ሆሆ ፡ እርሱን ፡ ተማመነ (፪x)
በውሃው ፡ ላይ ፡ እየተረማመደ ፡ እየተረማመደ
ለሚፈሩ ፡ እምነትን ፡ አስለመደ (፪x)
ማዕበሉም ፡ ወጀቡም ፡ የሚታዘዝለት
ይሄ ፡ ማነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)
አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፬x)
|