Kalkidan Tilahun/Yitayegnal Bezu Neger/Yebereket Amlak

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search


ዘማሪ ቃልኪዳን (ሊሊ) ጥላሁን
ርዕስ የበረከት አምላክ
አልበም ይታየኛል ብዙ ነገር


ምህረቱ ገነነ በላዬ (፪x)
ባርኮቱ ገነነ በላዬ (፪x)


የበረከት አምላክ መባረክን ያውቃል
እጁ ያጠግባል እጁ ያጠግባል (፪x)
የበረከት አምላክ መባረክን ያውቃል
እጁ ያጠግባል እጁ ያጠግባል
እጁ ያጠግባል የእኔ ጌታ እጁ ያጠግባል


ምህረቱ ገነነ በላዬ (፪x)
ባርኮቱ ገነነ በላዬ (፪x)


በቃ በቃ ክረምት አለፈ
በጋው መጣ የመከራው ዘመን
ሁሉ ተረሳ የመከራው ዘመን ሁሉ ተረሳ
ከዓለት ንቃቃቱ ወጥቻለሁ የኢየሱሴን ማዳን
አወራለሁ የኢየሱሴን ማዳን አወራለሁ
ከዓለት ንቃቃቱ ወጥቻለሁ ድምጼን ለጌታዬ
አሰማለሁ ድምጼን ለጌታዬ አሰማለሁ


የበረከት አምላክ መባረክን ያውቃል
እጁ ያጠግባል እጁ ያጠግባል
የበረከት አምላክ መባረክን ያውቃል
እጁ ያጠግባል እጁ ያጠግባል የእኔ ጌታ
እጁ ያጠግባል እጁ ያጠግባል


ምድረ በዳውን ኤደን በረሃውንም ገነት
አድርገኸዋል አድርገኸዋል
ድስታና ተድላ ምሥጋናና ዝማሬ
ለእኔስ ሰጥተሃል ለእኔ ሰጥተሃል (፪x)


በጐ ስጦታ ፍፁም በረከት
አንተ/ከላይ ነህና የብርሃናት አባት (፪x)


አመልከዋለሁ አመልከዋለሁ (፫x)


ምህረቱ ገነነ በላዬ (፪x)
ባርኮቱ ገነነ በላዬ (፪x)
ምህረቱ ገነነ በላዬ (፪x)
ባርኮቱ ገነነ በላዬ (፪x)