ክብር ፡ እሰጣለው (Keber Esetalew) - ቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(3)

ይታየኛል ፡ ብዙ ፡ ነገር
(Yetayegnal Bezu Neger)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

ክብር እሰጥሃልው ፡ ጌታዬ ፡ ክብር ፡ እሰጥሃልሁ
ክብር ፡ እሰጥሃልው ፡ አምላኬ ፡ ክብር ፡ እሰጥሃልሁ (፪x)
ለአንተ ፡ ላረገው ፡ የሚገባኝ
ብዙ ፡ ውለታ ፡ ብዙ ፡ አለብኝ
ግን ፡ በምን ፡ አቅሜ ፡ እመልሳለሁ
የምችለውን ፡ ክብርን ፡ እሰጣለሁ

ክብር ፡ እሰጥሃልው ፡ ጌታዬ ፡ ክብር ፡ እሰጥሃልሁ
ክብር ፡ እሰጥሃልው ፡ አምላኬ ፡ ክብር ፡ እሰጥሃልሁ (፪x)

እንዴት ፡ ብዬ ፡ እንዴት ፡ አስችሎኝ ፡ አሃ
ሳላመልክህ ፡ እውላለሁኝ
እንዴት ፡ ብዬ ፡ እንዴት ፡ አስችሎኝ ፡ ኦሆ
ሳላመልክህ ፡ እኖራለሁኝ

ክብር ፡ እሰጥሃልው ፡ ጌታዬ ፡ ክብር ፡ እሰጥሃልሁ
ክብር ፡ እሰጥሃልው ፡ አምላኬ ፡ ክብር ፡ እሰጥሃልሁ (፪x)

እጥፍ ፡ ድርብ ፡ ምሥጋና ፡ ሆሆ
እጥፍ ፡ ድርብ ፡ ክብር ፡ ሃሃ
ይገባዋል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆሆ (፪x)

ይገባዋል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆሆ
ይገባዋል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሃሃ

አንተ ፡ ታላቅ ፡ በኃይል ፡ ታላቅ
ሥምህ ፡ ታላቅ ፡ ሥራህ ፡ ታላቅ
አንተ ፡ ታላቅ ፡ በኃይል ፡ ታላቅ
ሥምህ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ሥራህ ፡ ታላቅ

ሠማያትን ፡ የሞላህ ፡ ሆሆ ፡ የሞላህ ፡ ሃሃ ፡ የሞላህ
ምድርንም ፡ የሞላህ ፡ ሃሃ ፡ የሞላህ ፡ ሆሆ ፡ የሞላህ
የቅርብ ፡ እንጂ ፡ የሩቅ ፡ አምላክ ፡ አይደለህ ፡ ሃሃ ፡ አይደለህ

አንተ ፡ ታላቅ ፡ በኃይል ፡ ታላቅ
ሥምህ ፡ ታላቅ ፡ ሥራህ ፡ ታላቅ
አንተ ፡ ታላቅ ፡ በኃይል ፡ ታላቅ
ሥምህ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ሥራህ ፡ ታላቅ

ቀና ፡ ብል ፡ አሻቅቤ
እግዚአብሔር ፡ አጠገቤ
እነሆኝ ፡ የሚለኝ
በምድርም ፡ እርሱ ፡ አለኝ

የቅርብ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ እንጂ
የሩቅ ፡ አምላክ ፡ አይደለህ
ሠማይና ፡ ምድርን ፡ የሞላህ (፪x)

ስለ ፡ እራሴ ፡ የምለው ፡ ምንም ነገር የለኝም
ስለ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ የምለው ፡ ፈጽሞ ፡ አላጣሁኝም (፪x)

አንተ ፡ ታላቅ ፡ በኃይል ፡ ታላቅ
ሥምህ ፡ ታላቅ ፡ ሥራህ ፡ ታላቅ
አንተ ፡ ታላቅ ፡ በኃይል ፡ ታላቅ
ሥምህ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ሥራህ ፡ ታላቅ