ከአንተ ፡ የሚበልጥ (Kante Yemibelt) - ቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(3)

ይታየኛል ፡ ብዙ ፡ ነገር
(Yetayegnal Bezu Neger)

ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

አዝ፦ ከአንተ ፡ የሚበልጥ ፡ ለእኔ ፡ ማንም ፡ የለም
አንተ ፡ ብቻ ፡ አምላኬ/አንደኛ ፡ ዘለዓለም
ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ
ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ (፪x)

በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ አመሰግናለሁ
በአንተ ፡ ሥም ፡ እጆቼን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አነሳለሁ
በቅበና ፡ በስብ ፡ እንደሚጠግቡት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ነፍሴ ፡ ትጠግባለች ፡ አምላኬ ፡ ያልኩትን

አዝ፦ ከአንተ ፡ የሚበልጥ ፡ ለእኔ ፡ ማንም ፡ የለም
አንተ ፡ ብቻ ፡ አንደኛ ፡ ዘለዓለም
ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ
ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ

ቅዱሳኑ ፡ ሁሉ ፡ እርሱን ፡ ወደዱት ፡ የእኔን ፡ ጌታ
ፊተኛ ፡ ቀዳሚ ፡ ሆሆ ፡ አንደኛ ፡ አድርጉት ፡ ሆ
አንተ ፡ ስትወደድ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ የእኔ ፡ ጌታ
የወዳጄ ፡ ወዳጅ ፡ ልቤን ፡ ያረካኛል

አዝ፦ ከአንተ ፡ የሚበልጥ ፡ ለእኔ ፡ ማንም ፡ የለም
አንተ ፡ ብቻ ፡ አንደኛ ፡ ዘለዓለም
ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ
ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ

ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር
ክብር ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
በጽድቅ ፡ የተሞላህ ፡ ሆሆ
ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነህና (፪x)

ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር
ክብር ፡ ይሁን ፡ አምልኮ
በጽድቅ ፡ የተሞላህ ፡ ሆሆ
ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነህኮ (፪x)

ላመልክህ ፡ እወዳለሁ
ላመልክህ ፡ እወዳለሁ
ላመልክህ ፡ እወዳለሁ ፡ ላመልክህ (፪x)

ላከብርህ ፡ እወዳለሁ
ላከብርህ ፡ እወዳለሁ
ላከብርህ ፡ እወዳለሁ ፡ ላከብርህ

እስትንፋስ ፡ ያላቸው ፡ ፍጥረታት ፡ ሁሉ
እንዴት ፡ አንተን ፡ አይተው ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ይላሉ
በቋንቋቸው ፡ ሁሉም ፡ ያመሰግናሉ
ክብር ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ተመሥገን ፡ ይላሉ

ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር
ክብር ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
በጽድቅ ፡ የተሞላህ ፡ ሆሆ
ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነህና (፬x)

ከክብርም ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ ይሁንልህ
ከምሥጋና ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ ይሁንልህ ፡ ይሁንልህ
ይሁንልህ ፡ ይሁንልህ (፬x)