Kalkidan Tilahun/Yitayegnal Bezu Neger/Del Del Yeshetegnal

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ቃልኪዳን (ሊሊ) ጥላሁን
ርዕስ ድል ድል ይሸተኛል
አልበም ይታየኛል ብዙ ነገር

የጸና ግንብ ነው የእግዚአብሔር ሥም
ወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆ
ወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆ (፪x)

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሜዳ አድርጌው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሰባብሬው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ይታየኛል ይታየኛል ብዙ ነገር
ያየሁትን አየዋለሁ አንድም አይቀር (፪x)

ጨካኝ አድርጐኛል ጠላቴ
ጀግና አድርጐኛል አባቴ
አልበገርም ለፍርሃት
አልፌያለሁኝ በእሳት

ለጌታዬ እኔ አልፈራም
ለኢየሱስ እኔ አልፈራም
ለአምላኬ እኔ አልፈራም
በፍፁም እኔ አልፈራም

ጻድቅ እንደ አንበሳ
ያለ ፍርሃት ይኖራል
ኃጥእ ግን ፈሪ ነዉ
ሳይነኩት ይሸሻል (፪x)

የጸና ግንብ ነው የእግዚአብሔር ሥም
ወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆ
ወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆ

ኧረ ተነሥ ጀግናው ተነሥ
ወንዱ ተነሥ የእቃ ጦርህን ሁሉ ልበስ
ኧረ ተነሽ ጀግና ተነሽ
ሴቷ ተነሽ የእቃ ጦርሽን ሁሉ ልበሽ

ማነው ጀግና ማነው ደፋር
ጐልያድን የሚዘርር
እኔ አለሁኝ እኔ አለሁኝ
ምድር /አገር/ ሁሉ አይሸበር (፪x)

ጠላቴ /ሰይጣን/ እንዳይተወኝ እየተነኮሰኝ
ይብሱን ኃይለኛ ኃይለኛ አደረገኝ (፪x)

ኃይለኛ አደረገኝ ኃይለኛ አደረገኝ

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሜዳ አድርጌው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሰባብሬው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ይታየኛል ይታየኛል ብዙ ነገር
ያየሁትን አየዋለሁ አንድም አይቀር (፪x)

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሜዳ አድርጌው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሰባብሬው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ (፪x)