አላገኘሁም ፡ ፈልጌ (Alagegnehum Felegie) - ቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(3)

ይታየኛል ፡ ብዙ ፡ ነገር
(Yetayegnal Bezu Neger)

ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ (ሊሊ) ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

አላገኘሁም ፡ ፈልጌ ፡ ፈልጌ
ለአንተ ፡ የምሰጠውን ፡ መስዋት ፡ አድርጌ (፪x)

እራሴን ፡ ሰውነቴን ፡ መሰዊያው ፡ ላይ ፡ ላኑርልህ ፡ አሃሃ
ቅድስና ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ሕያው ፡ መስዋት
ይሁንልህ ፡ ይሁንልህ (፪x)

አላገኘሁም ፡ ፈልጌ ፡ ፈልጌ
ለአንተ ፡ የምሰጠውን ፡ መስዋት ፡ አድርጌ (፪x)

ከፍ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ
ተከብሮ ፡ ያለ ፡ በሠማይ
ምሥጋና ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት
አምልኮ ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት
ዝማሬም ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት

የማይመረመረው ፡ ድንቅ ፡ ነገር
የማይቆጠረው ፡ ተዓምራት
(፪x)
ሁሉን ፡ ያደረገው ፡ ማነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
ይህ ፡ የሰራ ፡ ማነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ አሃ (፪x)

ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን (፬x)

አላገኘሁም ፡ ፈልጌ ፡ ፈልጌ
ለአንተ ፡ የምሰጠውን ፡ መስዋት ፡ አድርጌ (፪x)

እራሴን ፡ ሰውነቴን ፡ መሰዊያው ፡ ላይ ፡ ላኑርልህ ፡ አሃሃ
ቅድስና ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ሕያው ፡ መስዋት
ይሁንልህ ፡ ይሁንልህ

ኃይል ፡ የሌለውን ፡ ምንኛ ፡ ረዳኸው
ጥበብ ፡ ያጣውን ፡ ምንኛ ፡ መከርከው
የደከመውን ፡ ምንኛ ፡ አገዝከው
የተጣለውን ፡ ምንኛ ፡ አነሳኸው (፪x)

ረድኤቴ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ (፬x)

የረዳኝ ፡ የረዳኝ ፡ ጌታዬ
ባለውለታዬ ፡ ባለውለታዬ ፡ ባለውለታዬ (፪x)

ሕይወቴን ፡ የሞላህልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገንልኝ
ጉልበቴን ፡ ያጸናህልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገንልኝ
መንገዴን ፡ ያቀናህልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገንልኝ
ጽዋዬን ፡ የሞላህልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገንልኝ

አንተ ፡ እጅህን ፡ ትከፍታለህ
አሃ ፡ ትከፍታለህ ፡ ኦሆ ፡ ትከፍታለህ
ሕይወት ፡ ላለው ፡ ሁሉ ፡ መልካም ፡ ነገር
ታጠግባለህ ፡ ኦሆ ፡ ታጠግባለህ ፡ አሃ (፪x)

እንደገና ፡ አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞላው
ዓይኔም ፡ አየችው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው
እንደገና ፡ እንደገና ፡ አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞላው
ዓይኔም ፡ አየችው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው (፫x)
አምላኬ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው

ህልም ፡ ነው ፡ ወይ ፡ እውን ፡ እንዴት ፡ ይገርማል
እግዚአብሔር ፡ ሲሰራ ፡ አንድ ፡ ቃል ፡ ያበቃል (፪x)

ከፍ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ
ተከብሮ ፡ ያለ ፡ በሠማይ
ምሥጋና ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት
አምልኮ ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት
ዝማሬም ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት

ምሥጋና ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት
አምልኮ ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት
ዝማሬም ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት