Kalkidan Tilahun/LeEgziabhier Qelal New/Weha Weha Endayel
ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን አልበም ለእግዚአብሔር ቀላል ነው ርዕስ ውኃ ውኃ እንዳይል
ውኃ ውኃ እንዳይል ሕይወቴን አጣፍጠህ ይሄ ነው የማይባል ልዩ ጣዕም ሰጥተህ (2) መኖር አስመኘኸኝ መኖር መኖር አለኝ መኖር የሚያስወድድ ኢየሱስ ስላለኝ
ውኃ ውኃ እንዳይል ሕይወቴን አጣፍጠህ ይሄ ነው የማይባል ልዩ ጣዕም ሰጥተህ (፪x) መኖር አስመኘኸኝ መኖር መኖር አለኝ መኖር የሚያስወድድ ኢየሱስ ስላለኝ (፪x)
እንደገና አመልክሃለሁ (፫X) እንደገና አከብርሃለሁ (፫X)
ይበቃኝ ነበረ እስካሁን የባረከኝ አንተ አልበቃህም ዎይ ባርከኸኝ ባርከኸኝ (፪x) ይበቃኝ ነበረ ራስህን የሰጠኸኝ አንተ አልበቃህም ዎይ ሰጠኸኝ ሰጠኸኝ (፪x)
እንደገና አመልክሃለሁ እንደገና አሃአሃ እንደገና እሰጥሃለሁ እንደገና አሃአሃ
ገነት ገብቻለሁ እዚሁ ምድር ላይ አልጠብቅም ገና እስክሄድ ሠማይ ላይ (፪x) ገነቴ ኢየሱስ ነው እዚሁ ምድር ላይ እኔ አልጠብቅም ገና እስክሄድ ሠማይ ላይ (፪x)
እንደገና አመልክሃለሁ እንደገና አሃአሃ እንደገና አከብርሃለሁ እንደገና አሃአሃ
አልጠገብኩምና አልረካሁምና እኔ አመልክሃለሁ ዛሬም እንደገና አልጠገብኩምና አልረካሁምና አመሰግናለሁ ዛሬም እንደገና
እንደገና አመልክሃለሁ እንደገና አሃአሃ እንደገና አሃአሃ እንደገና አከብርሃለሁ እንደገና አሃአሃ እንደገና አሃአሃ (፪x)