From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ንጹህ ፡ ፍፁም ፡ ነውር ፡ የሌለህ (፪x)
አንተ ፡ ነውር ፡ የለህም
አንተ ፡ እድፈት ፡ የለህም
አንተ ፡ ጉድለት ፡ የለህም
አንተ ፡ እንከን ፡ የለህም (፪x)
አንተ ፡ ራስህ ፡ እውነት ፡ ነህ
ምንም ፡ ውሸት ፡ የለብህ
ኦ ፡ የለብህ (፪x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ንጹህ ፡ ፍፁም ፡ ነውር ፡ የሌለህ (፪x)
አንተ ፡ ነውር ፡ የለህም
አንተ ፡ እድፈት ፡ የለህም
አንተ ፡ ጉድለት ፡ የለህም
አንተ ፡ እንከን ፡ የለህም (፪x)
ታድያ ፡ እኔ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው
እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x)
አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው
እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x)
ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ
ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ
ፍርድንና ፡ ጽድቅን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ የሚያደርግ
እርሱ ፡ መሆኑን ፡ በማወቁ ፡ ብቻ
በዚያ ፡ ይመካ (፪x)
አውቄያለሁና ፡ ጠንቅቄ
ያላንተ ፡ ተስፋ ፡ እንደሌለኝ
ያላንተ ፡ ተስፋ ፡ እንደሌለኝ (፪x)
አንተን ፡ የታመነ ፡ ሰው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሳይደምር/ሳይጨምር
የተረጋገጠ ፡ ነው ፡ ፍጻሜው ፡ እንደሚያምር (፪x)
ታድያ ፡ እኔ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው
እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x)
አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው
እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x)
አዋቂው ፡ በዕውቀቱ ፡ አይመካ
ጻድቁም ፡ በጽድቁ ፡ አይመካ
ፀላይም ፡ በፀሎቱ ፡ አይመካ
ጿሚዉም ፡ በመጾሙ ፡ አይመካ
ፍርድንና ፡ ጽድቅን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ የሚያደርግ
እርሱ ፡ መሆኑን ፡ በማወቁ ፡ ብቻ
በእርሱ ፡ ይመካ (፪x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ንጹህ ፡ ፍፁም ፡ ነውር ፡ የሌለህ (፪x)
አንተ ፡ ነውር ፡ የለህም
አንተ ፡ እድፈት ፡ የለህም
አንተ ፡ ጉድለት ፡ የለህም
አንተ ፡ እንከን ፡ የለህም (፪x)
አንተ ፡ ራስህ ፡ እውነት ፡ ነህ
ምንም ፡ ውሸት ፡ የለብህ
ኦ ፡ የለብህ (፪x)
|